1 ሺህ 440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በድምቀት ተከበረ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 27 2011ማስታወቂያ
በበዓሉ በአዲስ አበባ ከተማም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፈቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተገኝተዉ ንግግር አድርገዋል።
በበዓሉ ተቀዳሚ ሙፈቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮዉ የኢድ አልፈጥር በዓል ሰላምና አንድነት የታየበት መሆኑን ገልፀዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች የኢድ ሶላት መስገጃ ቦታን ለህዝበ ሙስሊሙ በማፅዳት ላሳዩት ቀና ትብብር አመስግነዋል። 1 ሺህ 440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ከተማ በሚከናወኑ የፅዳት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የችግኝ ተከላ ስራዎች እንዲሳተፍ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሸገር እና አንበሳ የከተማ አውቶቡሶች ከተለያዩ የከተማዋ አቅጣጫዎች የኢድ ሶላት ወደ ሚደረግበት የአዲስ አበባ ስቴዲየም የደርሶ መልስ የነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት በትናንትናዉ ዕለት በፌስ ቡክ ገፁ ገልፆ ነበር።
ጌታቸዉ ተድላ
አዜብ ታደሰ