1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖሊስ የበተነው የመቀሌው ሰላማዊ ሰልፍ

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015

በሰልፈኞችና ሌሎች ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና ብርበራ እንዲሁም የጀምላ እስር በመቐለ ሮማናት አደባባይ፥ ወታደራዊ እና ሲቪል በለበሱ 'የፀጥታ ሐይሎች' ሲፈፀም ተመልክተናል። የዶቼቬሌ እና ቪኦኤ ዘጋቢዎች ላይም መለዮና ሲቪል በለበሱ ታጣቂዎች እንግልት፣ ንብረት መነጠቅ ብርበራና ስራ እንዳይሰሩ የመከልከል ሕገወጥ ተግባራት ተፈፅመዋል።

https://p.dw.com/p/4W5E7
የፖሊስ ልብስ የለበሱ እንዲሁም ድህንነት መሆናቸው የሚገልፁ ሌሎች አካላት በሰልፈኛ ወጣቶቹ ላይ በወሰዱት የሐይል እርምጃ ሰልፉ ተስተጓጉሏል። ሰልፈኞቹ "የዜጎች መብት ይከበር" ፣ "በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች መብት ይከበር" ፣ "ሰላማዊ ትግላችን እንቀጥላለን" ፣ "ጭቆና ይብቃን" የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮች ሲያስተጋቡ እና በፅሑፍ ሲያሳዩ ነበር።
ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የጀመረው ይህ ሰልፍ በመጀመርያ ዙር ሰልፉ የጀመሩ ወጣቶች በፖሊስ ከተወሰዱ በኃላ ተቀዛቅዞ የነበረ ቢሆንም በኃላ ላይ ሌሎች ወጣቶች የተለያዩ መፈክሮ ይዘው በመምጣት ሰልፉን አስቀጥለዋል። ምስል Million Haileselassie /DW

ፖሊስ በኃይል የበተነው የመቀሌው ሰላማዊ ሰልፍ

ዛሬ በመቐለ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ታጣቂዎች በሐይል ተበተነ። በሰልፈኞች እና ሌሎች ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና ብርበራ እንዲሁም የጀምላ እስር በመቐለ ሮማናት አደባባይ፥ ወታደራዊ እና ሲቪል በለበሱ 'የፀጥታ ሐይሎች' ሲፈፀም ተመልክተናል። የተቃውሞ ሰልፉ ጠርተው ከነበሩ ፓርቲዎች መካከል የሆነው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ እንዳስታወቀው እስካሁን ከ150 በላይ ስዎች ከሰልፉ ጋር በተገናኘ ታስረዋል። ሰልፉን ለመከታተል በመቐለ ሮማናት አደባባይ በተገኙ የዶቼቬሌ እና ቪኦኤ ዘጋቢዎች ላይም መለዮ እና ሲቪል በለበሱ ታጣቂዎች እንግልት፣ ንብረት መንጠቅና ብርበራ እንዲሁም ስራ እንዳይሰሩ የመከልከል ሕገወጥ ተግባራት ተፈፅመዋል።

 

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና የጠሩት እና ዛሬ በመቐለ የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የክልል የፀጥታ የተባሉ ሐይሎች በሐይል ሲበትኑት በበርካቶች ላይ የአካል ጉዳይ ደርሷል፣ በአጠቃላይ ከ150 በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ሌሎች የሰልፉ ተሳታፊዎች በፖሊስ መታሰራቸው ተመልክቷል። ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የጀመረው ይህ ሰልፍ በመጀመርያ ዙር ሰልፉ የጀመሩ ወጣቶች በፖሊስ ከተወሰዱ በኃላ ተቀዛቅዞ የነበረ ቢሆንም በኃላ ላይ ሌሎች ወጣቶች የተለያዩ መፈክሮ ይዘው በመምጣት ሰልፉ ቢያስቀጥሉትም የፖሊስ ልብስ የለበሱ እንዲሁም ድህንነት መሆናቸው የሚገልፁ ሌሎች አካላት በሰልፈኛ ወጣቶቹ ላይ በወሰዱት የሐይል እርምጃ ሰልፉ ተስተጓጉሏል። ሰልፈኞቹ "የዜጎች መብት ይከበር" ፣ "በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች መብት ይከበር" ፣ "ሰላማዊ ትግላችን እንቀጥላለን" ፣ "ጭቆና ይብቃን" የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮች ሲያስተጋቡ እና በፅሑፍ ሲያሳዩ ነበር። በሮማናት አደባባይ በነበረን ቆይታ በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ ፖሊሶች እና ሌሎች ሲቪል የለበሱ ታጣቂዎች ከፍተኛ ደብደባ ሲፈፅሞ፣ ከእነ የአካል ጉዳታቸው እና ደም እየፈሰሰባቸው ጎትተው ወደ መኪኖች ሲሰቅሉ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በአካባቢው ከነበረ ሰው ሲነጥቁ እና ሲበረብሩ ተመልክተናል። የሰልፉ አስተባባሪ ከነበሩት መካከል የጠየቅናቸው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አለምሰገድ አረጋይ እስከ ዛሬ ግማሽ ቀን ድረስ 50 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ከ1 መቶ በላይ የሰልፉ ተሳታፊዎች እና ሌሎች አካላት በፖሊስ መታሰራቸው ተናግረዋል።

ዛሬው ሁነት በትግራይ ያለው አገዛዝ አሁንም በቀድሞ ባህሪው ለመቀጠል ያለው ፍላጎት ማሳያ ሲሉ ነው ሲሉ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጨምረው ገልፀዋል።
ሰልፉ ለመከታተል ወደ ቦታው ባመሩ ጋዜጠኞች ላይም ከፍተኛ እንግልት ተፈፅሟል። ሰልፉ ለመከታተል በመቐለ ሮማናት አደባባይ በተገኙ የዶቼቬሌ ጨምሮ የቪኦኤ እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ የግል ሚድያ ዘጋቢዎች ላይም መለዮ እና ሲቪል በለበሱ ታጣቂዎች እንግልት፣ ንብረት መንጠቅና ብርበራ እንዲሁም ስራ እንዳይሰሩ የመከልከል ሕገወጥ ተግባራት ተፈፅመዋል። ምስል Million Haileselassie /DW

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ በዛሬው ሁነት ሰልፉ ለመከታተል ወደ ቦታው ባመሩ ጋዜጠኞች ላይም ከፍተኛ እንግልት ተፈፅሟል። ሰልፉ ለመከታተል በመቐለሮማናት አደባባይ በተገኙ የዶቼቬሌ ጨምሮ የቪኦኤ እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ የግል ሚድያ ዘጋቢዎች ላይም መለዮ እና ሲቪል በለበሱ ታጣቂዎች እንግልት፣ ንብረት መንጠቅና ብርበራ እንዲሁም ስራ እንዳይሰሩ የመከልከል ሕገወጥ ተግባራት ተፈፅመዋል። የዛሬው ሁነት በትግራይ ያለው አገዛዝ አሁንም በቀድሞ ባህሪው ለመቀጠል ያለው ፍላጎት ማሳያ ሲሉ ነው ሲሉ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጨምረው ገልፀዋል።

የዛሬው ሁነት በትግራይ ያለው አገዛዝ አሁንም በቀድሞ ባህሪው ለመቀጠል ያለው ፍላጎት ማሳያ ሲሉ ነው ሲሉ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጨምረው ገልፀዋል።
የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ትላንት ሰጥተውት በነበረ መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ 'መብት ነው' ብለው የነበረ ሲሆን ይሁንና የድህንነት ስጋት ስላለ ወደሌላ ግዜ እንዲዛወር የአስተዳደራቸው ፍላጎት መሆኑ ገልፀው ነበር።ምስል Million Haileselassie/DW

በሰልፉ፣ የፖሊስ የሐይል እርምጃ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከመቐለ ከተማ የፓሊስ አዛዥች መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ትላንት ሰጥተውት በነበረ መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ 'መብት ነው' ብለው የነበረ ሲሆን ይሁንና የድህንነት ስጋት ስላለ ወደሌላ ግዜ እንዲዛወር የአስተዳደራቸው ፍላጎት መሆኑ ገልፀው ነበር።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ