ፈረንሳይን ያስቆጣዉ የብሪታንያ የአዉስትራልያና የአሜሪካ ስምምነት
ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2014ማስታወቂያ
ከፕሬዝዳንት ባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ይሻሻላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአውሮጳ ህብረትና አሜሪካ ግንኙነት፤ አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ነው የሚታየውና የሚሰማው። ፕሬዝዳንት ባይደን በተለይ ከአውሮጳ ህብረት ጋር ወዳጅነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ሲገልጹ የነበር ቢሆንም፤ በቅርቡ በአፍጋኒስታን ጉዳይ በተናጠል የወሰዱት እርምጃና ባለፈው ሳምንት ደግሞ ከብሪታኒያና አውስትራሊያ ጋር የፈረሙት የሦስትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ግን ይልቁንም የህብረቱን እና አሜርካንን ግንኙነት የበለጠ እንዳሻያክረው አስግቷል። ፈረንሳይ የሦስትዮሹ ወታደራዊ ግንኙነት ቀጥተኛ ተጠቂ ናትም እየተባለ ነው።
አዜብ ታደሰ
ገበያዉ ንጉሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ