ጥሪ የተደረገላቸው የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2014ማስታወቂያ
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሀገርን ለመጠበቅ እገዛ እንዲያደርግ ያቀረበውን ጥሪ መንግሥት መቀበሉ አንዳስደሰተው የኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊት አባላትን ያሰባሰበው ማኅበር ገለጸ። ሀገርን ማስከበር፣ ሠራዊትን ማስተማር፣ ማሰልጠን እና ማገልገል የሚያስችል ብቃት እያለው እጅን አጣጥፎ መቀመጡ ተገቢ እንዳልሆነ በማመን፣ ለመንግሥት ያቀረብነው ጥያቄ ተመልሷል ያለው የቀድሞ ሠራዊት የድጋፍና የልማት ማኅበር፤ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ አመልክቷል። የቀድሞው ሠራዊት በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የማይደራደር መሆኑን የጠቀሱት የማኅበሩ ፕሬዝደንት የሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ፤ ሠራዊቱ ከውጊያ ባሻገር ልዩ ልዩ ተቋማትን በመጠበቅ ኃላፊነት የሚሠማሩ ወጣት የፀጥታ አካላት ወደ ግንባር እንዲሄዱ ለተቋማቱ ጥበቃ ሽፋን በመስጠትም ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ