1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ዐቢይ በነቀምት ከነዋሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2015

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ትናንት ተወያይተዋል ። የአካባቢው የልማትና ሰላም ጉዳይ ላይ ባተኮረው ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ «ሕዝቡ ሰላም በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የማድረግ የጋራ ኃላፊነት አለብን» ሲሉ በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው አመልክተዋል ።

https://p.dw.com/p/4QMDy
Äthiopien Stadt Nekemit | Premierminister Abiy Ahmed mit Vertretern der Wollega-Zonen Region Oromia
ምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia

«እድሉ ሊያመልጠን አይገባም»፦ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ትናንት ውይይት አድርገዋል ። የአካባቢው የልማት እና ሰላም ጉዳይ ላይ ባተኮረው ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ «ሕዝቡ ሰላም በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር የማድረግ የጋራ ኃላፊነት አለብን» ሲሉ በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው አመልክተዋል ። «የውስጥ ችግሮቻችን ከፈታን ሌላው ያሳስበናል ብዬ አላስብም» ያሉት ጠቅላይ ሚንሥትሩ፦ «እድሉ ሊያመልጠን አይገባም» ሲሉም ተደምጠዋል ። ወኪላችን ያነጋገራቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች በምዕራብ ኦሮሚያ ሠላም እንዲሰፍንና በጸጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጡ የልማት ሥራዎች እንዲቀጥሉ ለጠቅላይ ሚነስቴሩ ሀሳብ ማቅረባቸውን ጠቁመል ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ለውይይት ተቀምጠው
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ለውይይት ተቀምጠውምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ ነቀምቴ በትናንትው ዕለት ከሆሮ ጉደሩ ወለጋ፣ ከቀሌም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ የተሰባሰቡ ተወካዩች ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድና ሌሎች የፌደራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል ። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎችም ለ2 እና 3 ዓመታት የዘለቀው የፀጥታ ችግር መፍትኄ እንዲያገኙ እና ኅብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግሥት ዘላቂ መፍተኄ እንዲያበጅ ጠይቀዋል ። አቶ ገመቹ ኦላና በውይይቱ ላይ ከተሳተፉ መካከል ሲሆኑ፤ በሁሉም ዞኖች የልማት ስራዎች ወደኃላ መቅሬታቸውን፣በርካተታ ተጀምረው የነበሩ ፕሮጀክቶች በጸጥታ ችግር ምክንያት መቋረጣቸውን ጠቁመዋል፡፡

" እንደ ምዕራብ ኦሮሚያ ልማት በስፋት አለመኖሩን፣ የተጀመሩትም ልማቶች መቋረጣቸውን፣ ተጀምረው የነበሩ መንገዶ፣ኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ በከተማ ደረጃ ተጀምሮ የነበረው እንኳ ስራ ላይ አልዋለም፡፡ በጸጥታውም ዘርፍ  በክልልም ውስጥና አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ጸጥታ ችግሩን  ማረጋጋት ለምን አልተቻለም ብለን ለጠቅላይ ሚኒትስሩ ጥያቀአችንን አቅረበናዋል፡፡ "
የነቀምቴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ቶሌራ ምትኩም በውይይቱ ላይ ተሳተፈው የነበሩ ሲሆን በምዕራብ አሮሚያ በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ስራ ያቆሙ ፋብሪካዎች እንዳ እንዲሁም  በርካታ ተቋማት እንደወደሙ ጠቁመው ችግሩን በውይይት እንዲፈታ አመልክተዋል፡፡  "አራቱም ወለጋ ዞኖች ውስጥ ልማት እንደሚያስፈልግና የተቋረጡ በምን መልኩ መቀጠል ይችላሉ የሚሉ ጥያቀዌዎች ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም ያለው የጸጥታ ችግሮች እንዲፈቱ ሰውን የሚያፈናቅሉና በአዋሳኝ አካባቢዎችም ጥቃት የሚፈጽሙ ሀይሎች እንቅስቃሴም እንዲገታ ሀሳብ ቀርቧል፡፡"

በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ ነዋሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ለመወያየት ተቀምጠው
በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ ነዋሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ለመወያየት ተቀምጠውምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia

ጠቅላይ ሚስኒቴር ዶ/ር አብይ አህመድ "ያለ ሠላም ልማት የማይታሰብ" መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ታጣቂዎች በሰላም መግባት እንደሚችሉም በውይይቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙን እንደዘገቡት አካባቢው ባለው ሀብት ልክ የሚፈለገውን ያህል አለመልማቱን አብራርተዋል፡፡ " ከእኛ በተቃራኒ የተለየ ሀሳብ በማራመድ የሚትታገሉ ሰዎች የሚሰሩ መንገዶች እንዳይሰራ አታስቁሙ፣መንገዱ የሚሰራው ለህዝብ ስለሆነ ለህዝብ የምትታገሉ ከሆነ፡፡ መሰረተ ልማት እንዳይሰራ መከልከል ትክክል አይደለም፡፡ ሁላችን ጠብቀን ማሰራት ነው ያለብን፡፡ በሰላም በመታገል ሀሳባቸውን እና ፖሊሲአቸውን ለህዝብ ማቅረብ ይችላሉ" ብለዋል፡፡ 

በምዕራብ አሮሚያ የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግሮች በውይይት እንዲፈታ ምሑራንና የሀገር ሽማግለዎች ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡ በምእራብና ደቡብ ኦሮሚያ በስፋት የሚንቀሳቀሰው መንግስት ሼነ ብሎ የሚጠራው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራተዊት ብሎ የሚጠራ ታጣቂ ቡድን ገለልተኛ አካል በተገኘበት ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ከዚህ ቀደም አቋሙን ገልጸዋል ፡፡ 

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ