1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭቱ ወደ አፋር መስፋፋቱ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2014

የትግራይ ኃይሎች ትናንት ማለዳ በአፋር መዕከላዊ ዞን (ፈንቲረሱ) በከፈቱት ጦርነት የአከባቢው ንጹሃን በከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚለው መሐመድ ኑር እስካሁን ቢያንስ 3ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች ዱብቲ ሆስፒታል መድረሳቸውን ተመልክቷል፡፡ በርካታ ቁስለኞችም በአከባቢው ጤና ጣቢያ በመታከም ላይ መሆናቸውን መስማቱንም አክሏል፡፡

https://p.dw.com/p/4G37H
Äthiopien: Tigray-Krise reißt regionale Grenzstadt auseinander
ምስል DW

ግጭቱ ወደ አፋር መስፋፋቱ

ትናንት ዳግም የተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአፋር ማዕከላዊ ዞን በንጹሃን ላይ ጉዳት ማድረሱን የአይን እማኞች ገለጹ፡፡በአከባቢው ከባድ መሳሪያ ቤታቸው ላይ አርፎ ሁለት ልጆቻቸው የሞቱባቸው እናት በሪፌራል ዱብቲ ሆስፒታል መድረሳቸውን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች መረጃዎች ጠቁመዋል።የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገዓዝ አህመድ በፊናቸው ትናንት ንጋት አከባቢ በተከፈተው ጦርነት በአፋር ያሎ ወረዳ ሦስት ቀበሌያት በደረሰ ጥቃት እስካሁን ቢያንስ የሦስት ንጹሃን ዜጎች ህይወት መሰማቱንና ከ10 ያላነሱ ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለዶቼቬለ ገልጸዋል። ፡፡ በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን ኢሬብቲ ከተማ ተፈናቅሎ ሰመራ የሰነበተው ተፈናቃይ መሃመድ ኑር ዑስማን፤ ከወራት በፊት በአብዓላ በኩል የትግራይ ኃይሎች ስድስት ወረዳዎች ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ ከተፈናቀለ ወደ መደበኛ ስራው አልተመለሰም፡፡ ይልቅ በጦርነቱ የተጎዱ ንጹሃንን በመታደግ ስራ ላይ ተሰማርቶ የበጎፈቃደኝነት ተግባርን እያከናወነ ይገኛል፡፡ መሃመድ ኑር እንደሚገልጸው የትግራይ ኃይሎች ትናንት ማለዳ በአፋር መዕከላዊ ዞን (ፈንቲረሱ) በከፈቱት ጦርነት የአከባቢው ንጹሃን በከባድ መሳሪያዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። መሃመድ ኑር እንደሚለው እስካሁን ቢያንስ ሶስት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች ዱብቲ ሆስፒታል መድረሳቸውን በአይኑ ተመልክቷል፡፡ ሌሎች በርካታ ቁስለኞችም በአከባቢው ባለው ጤና ጣቢያ በመታከም ላይ መሆናቸውን መስማቱንም አክሏል፡፡

የአፋር ሰዓብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገዓዝ አህመድ በበኩላቸው ትናንት ማለዳ ባገረሸው ጦርነት ቢያንስ የሦስት ንጹሃን ሰዎች ሞት መረጋገጡን ያነሳሉ፡፡ ትናንት ማለዳ የተከፈተው የከባድ መሳሪያ ተኩስ እሩምታ እስከ አመሻሹ 2፡00 ገደማ ቀጥሎ እንደነበርና ዛሬ ጠዋትም እስከ ረፋድ ጦርነቱ እንደነበርም አቶ ገዓዝ ከአከባቢው በሚደርሳቸው መረጃዎች ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል፡፡ አቶ ገዓዝ  አክለውም የትግራይ ሃይሎች አሁን ጦርነት የከፈቱበት የአፋር ማዕከላዊ ዞን ከዚህ ቀደም ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው የሚባለውን «ጭፍራ»ን ተቆጣጥረው ሚሌንም የመቆጣጠር ፍላጎት ያሳዩበት ስፋራ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶ እንደነበርም በማስታወስ አሁንም ጦርነቱ ከገፋ ሌላ አሰቃቂ ሰብዓዊ ቀውስ ሊከተል እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ትናንት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ኃይሎች በምስራቅ ግንባር በቢሶበር፣ በዞብል እና በተኩለሽ አቅጣጫዎች ጥቃት ፈጽመዋል” ብሎ ነበር፡፡ የትግራይ ኃይሎች በፊናቸው የፌዴራልና የክልል ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ ዞን በኩል ከባድ ጦርነት ከፍተውብኛል ሲሉ ወቅሰው ነበር፡፡

ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ