ጋዛ ከግብፅ የሲና በረሐ በስተሰሜን፣ ከሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ የሚገኝ እና 363 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሰፋ የፍልስጤም ግዛት ነው። በእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ በጋዛ ሠርጥ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሚሊዮኖች በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል። በግዛቲቱ በተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ እስራኤል ብርቱ ውግዘት ደርሶባታል።