አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በተለይ ለዶቼ ቬለ አረጋገጠ። በሚዲያ ተቋሙ የሚያገለግለዉ ጋዜጠኛ ኡስማን ኡኩሚ እንደገለፀዉ ፤ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የስርጭት ጣብያም ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብሎአል።
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በተለይ ለዶቼ ቬለ አረጋገጠ። በሚዲያ ተቋሙ የሚያገለግለዉ ጋዜጠኛ ኡስማን ኡኩሚ እንደገለፀዉ ፤ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የስርጭት ጣብያም ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብሎአል። ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በሰራው ዘገባ ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። ዘግየት ብሎ በወጣ መረጃ ተይዘዉ የነበሩት አንዳንድ ጋዜጠኞች ተለቀዋል። በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ኔት ወርክ ጋዜጠኛን ከስርጭታችን በፊት አናግረነዉ ነበር።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ