ሕግ እና ፍትሕ
ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስትን ሊከስ ነዉ
ረቡዕ፣ የካቲት 4 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕግ ማሕበረሰብ ለዕድገት የተባለዉ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብአዊ መብት ጥሰትን በቸልተኝነት በማለፍ ወንጀል እንደሚከስ አስታወቀ።ከዚሕ ቀደም ብዙም የማይታወቀዉ የሕግ ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት በሕግ የተጣለበትን የዜጎችን ደሕንነት የማስከበር ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም።የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ንዋይ ግርማ እንዳሉት ድርጅታቸዉ በመንግሥት ላይ የሚመሰርተዉን የክስ ፋይል በቅርቡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለመክፈት አቅዷል።የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ክሱን ለመመርመር ካቅማሙ ጉዳዩን ለአሐጉር አቀፍ ተቋማት አድርሶ መንግሥትን ሊሞግት ዝቷልም።ርዕሠ-መንበሩን ባንጁል-ጋምቢያ ላደረገዉ የአፍሪቃ የሠብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤት ማለቱንም አስታዉቋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ