ድርድሩ አበቃ፣ ግን ይቀጥላል
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 7 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግድብ ምክንያት ከግብፅ ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የኢትዮጵያ፣የሱዳንና ግብፅ ባለስልጣናት ለአስራ አንድ ቀናት ያደረጉት ድርድር እንደከዚሕ ቀደሞቹ ሁሉ ያለ ሁነኛ ሥምምነት አብቅቷል።በድርድሩ ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ የቴክኒክ ቡድን ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌድዮን አስፋዉ እንደሚሉት ግን ተደራዳሪዎች ለፊርማ ከሚያበቃ ስምምነት ላይ ባይደርሱም የተስማሙባቸዉ ጉዳዮች አሉ።ኢንጂነር ጌድዮን በአፍሪቃ ሕብረት አደራዳሪነት የሚደረገዉ ድርድር ወደፊት ይቀጥላል ብለዉ ይገምታሉ።ኢትዮጵያ ግድቡን ዉኃ መሙላት ጀምራለች ለሚለዉ ጥያቄ ግን ኢንጂነሩ «የግድቡ ቁመት በጨመረ ቁጥር፣ ሙሌቱም ይጀመራል» በማለት አልፈዉታል።ኢንጂነር ጌድዮንን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ