ዴንማርክ፤ የአይሁዳዊያን ምኩራብ ፊት ለፊት ተኩስ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ዴንማርክ፤ የአይሁዳዊያን ምኩራብ ፊት ለፊት ተኩስ

ኮፕንሐግን በሚገኝ አንድ የአይሁዳዊያን ፀሎት ቤት ፊት ለፊት ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ቆሰሉ። የዴንማርክ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከቁስለኞቹ መካከል ሁለቱ ፖሊሶች ናቸው። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ፖሊስ በእግሩ እንደሸሸ የተነገረውን ተጠርጣሪ ማግኘቱን እና መግደሉን ይፋ አድርጓል።

እንደ ፖሊስ ገለፃ ተጠርጣሪው የአይሁዳዊያን ምኩራብን ሲጠብቅ ለነበረ ወጣት ሞት ተጠያቂ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በፖሊስ የተገደለው ተጠርጣሪ ይህ ከመሆኑ ከሰዓታት በፊት በአንድ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የ55 ዓመት ሰውንም ሳይገድል አልቀረም ተብሏል። በስብሰባው ላይ የተከፈተው ተኩስ ምናልባትም ኢላማ አድርጎ የነበረው ላርስ ቪልክስ የተባሉ የስላቅ ስእሎች ሰዓሊ ላይ ሳይሆን እንዳልቀረ ፖሊስ ገልጿል። ስዊዲናዊው ሰዓሊ ነብዩ መሐመድን የሚመለከቱ ስላቃዊ ምስሎችን ይስላሉ በሚል በተደጋጋሚ በሙስሊሞች ዘንድ ወቀሳ ቀርቦባቸው እና የጥቃት ኢላማም ሆነው እንደነበር ተገልጿል።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ