ዩናይትድ ስቴትስ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2014ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እንዲቻል ዲኘሎማሲያዊ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ዐስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ተዓማኒነት ያለውና ሁሉንም ያሳተፈ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀምር ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥት በጦርነቱ የህወሃት ኃይሎችን ድል አድርጎ ከእየ አካባቢዎቹ ማስወጣቱን ሲገልጥ፤ ሕወሓት ከአማራ እና ከአፋር ክልል የወጣሁት ለ«ሠላም» ነው ይላል። ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲገታ መጠየቋን እንደምትገፋበት ዐስታውቃለች። ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደረግም መንግሥትን መጠየቋን ገልጣለች።
ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ