1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በአሜሪካ ጥሪ አቀረበ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 14 2016

የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ለማስቆም የተደረሰው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በሰሜን አሜሪካ ጥሪ አቀረበ። ማኀበሩ፣ባወጣው መግለጫ ፣"የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መተግበር፣ለዘላቂ ሰላማችን ዋስትና ነው ብሏል።"

https://p.dw.com/p/4e3dE
የፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት ሲፈረም
በደቡብ አፍሪካ የተፈረው ግጭት የማቆም ሥምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር ጥሪ አቀረበምስል SIPHIWE SIBEKO/REUTERS

የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በአሜሪካ ጥሪ አቀረበ

በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር/ማተሰአ/፣ሰሞኑን ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ባወጣው መግለጫ፣የፕሪቶሪያው ስምምነት  የትግራይ ህዝብና ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ወደ ዘላቂ ሰላም ይመራናል ብለው ተስፋ ያደረጉት የሰላም ስምምነት መሆኑን አውስቷል። ይሁንና፣ይህን ስምምነት ላለመተግበርና ለማደናቀፍ የተለያዩ መሰናክሎችና ሴራዎች ሲሸረቡ እያየን ነው ሲል ወቅሷል።

የስምምነቱ አተገባበር መጓተት

ይህን መግለጫ አሁን ማውጣት ያስፈለገው፣የስምምነቱ አፈጻጸም በመጓተቱ መሆኑን የማኀበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘአማን አለምሰገድ ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል። "በተለይ አሁን  ችግሩ እየተጓተተ ስለመጣ፣ ጉዳዩ ወደ አፍሪቃ ህብረት እና ወደ አሜሪካ ወደ አሸማጋዮችና ዋስትና  ወደሰጡት ኀይሎች ወደእነዚህ አካላት ሄዷል።"

አቶ ሙሉ አሰፋ የማኀበሩ ኦዲተር ሲሆኑ ነዋሪነታቸው  ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ነው። በሰላም ስምምነቱ ብዙ ተስፋ አድርገው እንደነበር ይናገራሉ።

በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር ዋና ጸሐፊ አቶ ዘአማን አለምሰገድ
በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር ዋና ጸሐፊ አቶ ዘአማን አለምሰገድ በሥምምነቱ መሠረት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው አለመመለሳቸውን ጠቅሰዋልምስል Privat

የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ግምገማ

"መጀመሪያ የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲመጣ እኛ ነን መጀመሪያ መግለጫ ያወጣነው።ይህ ለሰላም የተደረገ ሂደት በጣም ጥሩ ነው እና ለሰላም እኛ በአቅማችን ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለን መግለጫ አውጥተናል።እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መቀበል አለብን ብለን የዚያን ጊዜ ብዙ የተለያዩ ዐሳቦች ይመጡ ነበር እና እኛ አቋም ወስደን እንደዚህ አድርገናል።አሁን ተስፋ እያደረግን ሂደት ላይ ነው እያልን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ተወላጆችን ሰብስበው ያደረጉት ንግግር በጣም ተስፋ የሚያስቆርጥና ይህን መግለጫ እንድናወጣ የገፋፋን እሱ ነው።"

አቶ መሉ፣ ለዚህ ምክንያታቸውን በዚህ መልኩ ገልጸውታል።

" ምክንያቱም አምና ክረምት እነዚህ ተፈናቃዮች ከክረምት በፊት ያርሳሉ ይሄዳሉ እየተባለ ተስፋ አድረገንግ ነበር እርሱ አለፈ።አሁንም ክረምት እየገባ ነው እና ተፈናቃዮቹ መመለስ አለባቸው።"

የማኀበሩ መግለጫ፣በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የፕሪቶሪያ ስምምነት ያለአንዳች መስተጓጎልና መሸራረፍ ተግባራዊ እንዲሆን ከትግራይ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ አሳስቧል።

ስለ ፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት የህወሓት መግለጫ

የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መተግበር ለዘላቂ ሠላም  ዋስትና መሆኑን፣ የማኀበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘአማን አስረድተዋል።

"የዚህ የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ መሆነ በጣም  አንገብጋቢ ነው፣በጣም አስፈላጊ ነው። ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ የሚችለውም ደግሞ ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ  ተግባራዊ ሲሆን ስለሆነ አሁን ለዚህ ነው ለተግባራዊነቱ ጥሪ የምናቀርበው።"

የተፈናቃዮች ተቃውሞ በትግራይ
በጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎች በፕቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት መሠረት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አበክረው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ምስል Million Haileselassie/DW

 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ህወሓት፣የትግራይ ሰራዊት አመራሮች፣ የትግራይ የኃይማኖት መሪዎችና የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በትግሉ ወቅት የነበረውን አንድነተቸውንና አብሮነታቸው አድሰው፣ማኀበሩ የጥፋት ሴራ ያለውን እንዲያከሽፉና በጽናት እንዲታገሉ እንዲሁም ጊዜውን የሚዋጅ አመራር እንዲሰጡም ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካው ልዩ ልዑክ ለኢትዮጵያ ሰላም ዘላቂ ሰላም ያመጡ ይሆን?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስለፕሪቶሪያው ስምምነት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ባለፈው ሳምንት ባካሄዱት ውይይት ስለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በተመለከተ የሚከተለውን ተናግረው ነበር።

"የፕሪቶሪያው ስምምነት ብዙዎቻችሁ አንሰታችኇል።በፕሪቶሪየው ስምምነትየተፈናቀሉ ከመመለስ ውጭ ከዲዲአር ውጭ ከሚገባው በላይ ነው የሄድነው።ተገምግሟል ፕሪቶሪያ በቀደም።" ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ 

እሸቴ በቀለ