1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የነቀምቴ ጉዞ እና የትግራይ ክልል መንግስት ለRSF ምላሽ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2016

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ ወደ ነቀምቴ ከተማ አቅንተው ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር ማድረጋቸው ፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ RSF የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ኃይሎች ከሱዳን ብሄራዊ ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባብሏል።

https://p.dw.com/p/4fiBX
Äthiopien Premierminister Abiy Ahimed Diskussion
ምስል Office of Prime minister of Ethiopia

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ዝግጅት

 የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ ወደ ነቀምቴ ከተማ አቅንተው ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር ማድረጋቸው ፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ አር ኤስ ኤፍ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች  ከሱዳን ብሄራዊ ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማስተባበሉን በተመለከተ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተንሸራሸሩ መልዕክቶችን ተመልክተናል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከትናንት በስትያ ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ሳይጠበቅ ወደ ነቀምቴ ተጉዘው ከአራቱ የወለጋ ዞን ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ነቀምቴ ስቴዲየም  እንዲህ በይፋ ለህዝብ ንግግር ሲያደርጉ ይኸ ሁለተኛቸው ነው።

ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት

ጠቅላይ ሚንስትሩ አምስቱን ዓመታት በግጭት ጦርነት ውስጥ ለነበረው ህዝብ ባደረጉት ንግግር “ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፤ ትናንትና ታግለን በደማችን አሸንፈናል” ብለዋል። በአካባቢው መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር እያደረገ ያለውን ጦርነት ባብቂያ ማግኘት እንዳለበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለድል የሆነው ሕዝብ ድሉን ይጠብቃል እንጂ እንደገና ወደ ጦርነት አይገባም” ነበር ያሉት ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ነቀምቴ መጓዝ እና ያደረጉትን ንግግር በተመለከተ በርካቶች ሃሳባቸውን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሲቀባበሉ ነበር።

ከእነዚህ ውስጥ በላቸው ዲባባ የተባሉ አስተያየት ሰጭ ያሰፈሩትን እና ሰለሞን ታደሰ የተባሉ ደግሞ ለበላቸው አስተያየት የሰጡትን መልስ ስናስቀድም በላቸው እንዲህ ይላሉ

«ሠላም ለማውረድ እዛ ድረስ መሄድ አስፈላጊ አይደለም ፤ መልዕክቱ ይገባናል ከአካባቢው የኦነግ ጦር አጥፍቻለሁ ሠላም ነው ለማለት ነው ፡፡ ወዳጄ ግልፁን ልንገርህ ኦነግን ጫካ ውስጥ ብቻ አትፈልገው ፡፡ እውነቱ ኦነግ ያለው በኦሮሞ ህዝብ ልብ ውሥጥ ነው ያን በፍፁም አታጠፋውም፡፡ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ የወለጋ ጉብኝት አስተያየት

ሌላው እውነት በፍፁም -- በፍፁም የኦሮሞን ህዝብ ልታጠፋው አትችልም፡፡» ሲሉ ሰለሞን ታደሰ ለዚሁ አስተያየት በሰጡት ምላሽ እንዲህ ብለዋል።

«እኔ ጋር ኦነግ በልቤ ዉስጥ የለም ስለዚህ ወዳጄ ስለራስ ብቻ ተናገር እኔ የማቀዉ ኦነግ ለሆሮሞ ሕዝብ የቆመ ለሕዝብ የሚያስብ ነዉ ያዉኑ ትጥቅ ይዞ የሚታገለዉ ሌባ ዘራፊ የሆሮሞን ሕዝብ ያሰቃየ የገደለ የዘረፈ ሽፍታ ነዉ ለዚህ ደሞ ከእኔ በላይ ምስክር የለም በቦታዉ ስላለሁ» ብለዋል።

የነቀምቴ ከተማ
«ሠላም ለማውረድ እዛ ድረስ መሄድ አስፈላጊ አይደለም ፤ መልዕክቱ ይገባናል ከአካባቢው የኦነግ ጦር አጥፍቻለሁ ሠላም ነው ለማለት ነው»

ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚል ስም በፌስ ቡክ በሰፈረ ሃሳብ ·

መሪዬ ዋሸህ እኔ ኢትዮጲያ ውስጥ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ተመልሶል ብዬ አላምንም ፤ ይላሉ ኢትዮጲያ ውስጥ አሁን ላይ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በጉልበት የሚተዳደር እንጂ ፈቅዶና ወዶ የሚተዳደርም የሚያስተዳድርም የለም !

እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እሩቅ ሳንሄድ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ  አዲስ አበባ ላይ ተግባራዊ አልተደረገም ፤ አዲስ አበባ ላይ ያልተገበርከውን እራስን በራስ የማስተዳደር መብት በሸሻ ላይ ተግብሬዋለሁ ብትለኝ አላየሁም አልሰማሁም ከማለት  ከማለት ውጪ ምንም አልልህም ብለዋል።

ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ የወለጋ ጉብኝት አስተያየት

 

እውነት ይናገር በሚል የፌስ ቡክ ስም በሰፈረ ሃሳብ

«አባቱ ጠቅላዩ ወላ ተጠራጠርከው/ ወላ አመንከው ትዝ አይለውም! እናንተ መከራ በላችሁ እንጂ ለዘገምተኛ አስተሳሰቦች ቦታ እንደማይሰጥ እስካሁንም ካልገባችሁ ያው…. »በማለት  ሃሳባቸውን ገትተዋል።

ሳም ፉድ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው

«ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ክልል ፕሬዝዳንት እንጂ የሀገር መሪ መስለው አልታዩም በተለይ ባለፉት ዘመናት የኦሮሞ ህዝብ በቀኝ ተገዝቶ ነበር ያሉት በጣም አደገኛ ንግግር ነው። »ብለዋል።

“ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤ ለዚህ አንታገልም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

እዩኤል ንጉሴ ደግሞ ለውጡን ለመደገፍ ወጣ የተባለውን ህዝብ አስመልክተው ባሰፈሩት ሃሳብ

«የድጋፍ ሰልፍ ነው ወይስ እንግዳ ተቀበል ተብሎ ከየቤቱ እንዲወጣ በካድሬ የታዘዘ ሕዝብ ? »በማለት ስላቃዊ ጥያቄ ጠይቀዋል።

 ወፍ የለም በሚል ስም በሰፈረ ሃሳብ ደግሞ

«አሁንላይ ለኦሮሞ ህዝብ የአመራር / የሰው / ለውጥ / ተደረገለት እጅ ህይወቱን የቀየረለት ለውጥ የለም ባለበት ነው ግንደግሞ ኦሮሞ ኦሮሞ እያላችሁ በስሙ ትነግዳለችሁ ። »ይላል።

ኢማን ኢማም የተባሉ አስተያየት ሰች በበኩላቸው  ባሰፈሩት ሃሳብ

ነፃ መውጣት ማለት ህዝብ የፈለገውን ፓርቲ ሲመርጥና ፖለቲከኛውም በአመለካከቱ አለመገደሉ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።እኔ ብቻ ነኝ የማውቅልህ ግን ፈፅሞ አዋቂነት አይደለም።የሚያሳዝነው ግን የኦሮሞ መጨፍጨፍ አለመቆሙ ነው።

የአደባባይ ሰልፍ ጉዳይ

 ወንዲ ወንዲ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ አደረጉ የተባለው ንግግር በተከላከሉበት አስተያየታቸው

ምንም የሚያሻማ ነገር የተናገረ አይመስለኝም ይህ ሠው በዛ አካባቢ የኦሮሞን ህዝብ ነፃ እናወጣሀለን እኛ እናውቅልሀለን እያሉ እሚታገሉ የሸኔ አባላት እንዳሉ ሁሉም እሚያውቀው ጉዳይ ነው ስለዚህ ይህ ንግግር በቀጥታ(ሸኔዎችን) እነሡን እንዲቃወሙ የተደረገ ንግግር ነው ብለዋል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ አር ኤስ ኤፍ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች  ከሱዳን ብሄራዊ ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባብሏል ። የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ክስን አጣጥሎ ያወገዘው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፦ ሕወሓት ላይ የቀረበው ክስ  የሱዳንን ግጭት ዓለም አቀፋዊ መልክ ለማስያዝ ያለመ ብሎታል ። የአር ኤስ ኤፍን ክስ እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ማስተባበያን በተመለከተ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተስተናገዱ አስተያየቶች መካከል ተከታዮቹ ይገኙበታል።

የህወሃት አርማ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ አር ኤስ ኤፍ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች  ከሱዳን ብሄራዊ ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባብሏል ።ምስል Million Haileyessus/DW

ስዩም መኮንን የተባሉ አስተያየት ሰጭ ባሰፈሩት ሃሳብ

«እነሱ ይበሉ እንጂ ሁኔታው እውነት ሊሆን ይችላል፡ ምክንያቱም ያኔ በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያ ይልቅ ሱዳን ይቀርበናል/ ይበልጥብናል በለው ነበር።» ሲሉ አባዲ ወልደገብርኤል ምስግና በበኩላቸው

«ሊሆን ይችላል ግን የሱዳን ህዝብ ነው ለዘላለም የምኖረው እንጂ ገዥው ፓርቲ አይደለም» የሚል ሃሳብ አስፍረዋል።

አነ በላይ በሚል ስም በሰፈረ ሃሳብ ደግሞ

«አይ እናንተ መች ይሆን ራሳችሁን የምትችሉት። ትግራይን ካላነሳችሁ አይሆንላችሁም አይደል?።» ውንጀላውን አጣጥለዋል እዩኤል አክሊሉ በበኩላቸው

«ትግራይ አገር ናት? ነው ወይስ ጠቅላዩ ካሁኑ አድስ አበባ ብቻ ከመራሁ ይበቃኛል አሉ » በማለት የትግራይ ክልl አስተዳደር በቀ,ጥታ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሰጠውን ምላሽ በተመለከተ ሃሳባቸውን አስፍረዋል።

ሕወሓት ከሱዳን ጦር ጋ ወግኖ እየተዋጋ ነው መባሉን አስተባበለ

ባርኮት መሃሪ «ለምንድነው የትግራይ ወጣት ለሱዳን የሚሞተው ምንስ ሊያገኝ ነው? ይህ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው !» ሲሉ በህወሃት ላይ የቀረበውን ክስ አስተባብለዋል።

ሃዱሽ አዛናው ጸለምቲ በበኩላቸው

«ህወሓት ሰራዊት የለውም፣ የትግራይ ሰራዊት ከሆነ TDF ነው የሚባለው ተልዕኮውም የትግራይን ህዝብ መጠበቅ እንጂ ሌላ ተልዕኮ የለውም። RSF ሰሞኑ በኣልቡርሃን ለደረሰበት ከባድ ምት ሰበብ መፈለግ መሆኑ ነው።» ብለዋል።  

አይዞን በርታ  በሚል ስም በሰፈረ ሃሳብ ደግሞ «የአሜሪካ ካርዶች በተፈለገው በኩል ይመዘዛል ! አይጥ በበላው ዳዋ ተደበደበ አለ ያገሬ ሰው ። የላከው ያስታጠቀው ማን ሆነ የዋይታውስ አሻጥር ይህን ይመስላል።» ብለዋል።

በትግራይ በጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎች የመመለስ ዕቅድ

ሱራፌል ጥበቡ በበኩላቸው « ይሄ ሰውሄ አሉ ጄኔራል ሃምዳን ዳጋሎን መሆኑን ነው ፤ « አሜሪካ ለምታራምደው ፖለቲካ ስለማይመች በሰብአዊ መብት ስም በተከፈተቱት ድርጅቶቿ በኩል ስም ማጥፋት ተያይዘዋለች ይሄ ሰውዬ ዳርፉር ላይ ጭፍጨፋ በመፈፀም  ከአል በሽር ጊዜ ጀምሮ ይወቀሳል ነገር ግን አሁን መጮህ ያስፈለገው ጦሩ እየገፋ ስለሆነ ነው » የሚል አስተያየት አጋርተዋል።

ማግምሃ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው

«እንደዛ በል ተብሎ እንጂ በሆኑ አካሎች ፍ ቲዲኤፍ መጠራቱ ካባድ ዋጋ ያሰከፍለዋል ፤ የራሱን ዜጋ የሚደፍርና የሚገድል ቡድን  መሆኑን ብዙዎቹ ያረጋገጡት ነው ሲገረፍ የወያኔ እጅ አለበት መባሉ ከማን እንደተቀበለው አጀንዳው  መመርመር አለበት » ብለዋል።

ታምራት ዲንሳ 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር