የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይና የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት
ረቡዕ፣ መስከረም 6 2013ማስታወቂያ
ትናንት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት የተካሄደው እና በመጪው ሳምንት ይቀጥላል የተባለውን ውይይት የምመራው ከሆነ በጋራ ምክር ቤቱ የታቀፉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ አደርጋለሁ ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የተካሄደው ውይይት ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር ላይ ያተኮረ እንደነበር ያነጋገርናቸው ተሳታፊ ፓርቲዎች ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በነበረው ስብሰባ ላይ ሀምሳ ፖለቲከኞች ብቻ መሳተፋቸውም ታውቋል። ፓርቲዎቹ በቀጣይም በሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት፣ በምርጫ እና መሰል ጉዳዮችን ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ