1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጉራጌ የክልልነት ጥያቄ የህልውና ነው

ሰኞ፣ መጋቢት 18 2015

«የከተማዋን ነዋሪ የማይወክሉ ሰዎች የገቡበትን ስብሰባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መርተው የወጡት በዚህም ህብረተሰቡ ደስተኛ አይደለም» የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ

https://p.dw.com/p/4PKOG
Äthiopien Gurage Streik
በወልቂጤ ከተማ ከቤት ባለመውጣት አድማ የዘጉ የንግድ ሱቆች ምስል privat

በጠቅላይ ሚንስትሩ የወልቂጤ ጉብኝት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

Äthiopien Gurage Streik
የጉራጌ ማህበረሰብ የክልልነት ጥያቄ በተቃውሞ ሲያሰማ ምስል privat

 ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ቅዳሜ እረፋድ ከደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተገኝተው  ቢወያዩም ማህበረሰቡ የጠየቀውን እና እየታገለ ያለበትን ጉዳይ ምላሽ አልሰጡንም ሲሉ ደቼ ቬሌ ያነጋገራቸው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። እንደነዋሪዎቹ ገለፃ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ መምጣት በትግላችን ቀጣይነት ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት ለውጥ የለም ብለዋል። የጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ለደህንነቱ ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተዘጋጀው መድረክ  የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ አልነበረም   ብሏል « ሁለት አመት ሙሉ  ስንታሰር ሀብት ንብረታችን ሲወድም  ስንገደል  ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የት ነበሩ » ሲል አያይዞም የመጡት ለማሾፍ ነው ብሏል ስለተዘጋጀው የውይይት መድረክ ሲናሀር መድረኩ ጤነኛ አልነበረም ብሏል «እስከመጨረሻው የክልልነት ጥያቄያችን አይቆምም ከመንግስት ግን ምንም ነገር አንጠብቅም » ብሏል። የጉራጌ ህዝብን ማታለል አይቻልም ከዚህ በፊትም ከዚህ በኃላም  «ለጉራጌ የክልልነት ጥያቄ የህልውና ነው ወንድሞቻችን የሞቱበት በርካቶች የታሰሩ እና የተሰቃዩበት ነው »ሲል ለዶቼ ቬሌ ተናግሯል ።

 ሌላው የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ በቅዳሜው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር በነበረው ስብሰባ ህብረተሰቡ ደስኛ  አይደለም ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደከተማዋ በመጡበት ወቅት የአካባቢው ነዋሪ በሩን ዘግቶ መቀመጡ አንዱ ማሳያ ነው ሲል ተናግሯል ።«የከተማዋን ነዋሪ የማይወክሉ ሰዎች የገቡበትን ስብሰባ ነው መርተው የወጡት በዚህም ህብረተሰቡ ደስተኛ አይደለም» ሲል ትግሉ ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ ብሏል «በቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ እና ምንም ጥያቄ የምንመልስበት አይደለም ብለዋል «እስከጥግ ድረስ ትግል ይደረጋል እስከሞት ድረስ እያለነው ህዝቡ ያለው » አንድና አንድ  ጥያቄያችን ክልልነት ነው ክላስተር አይታሰብም ብለዋል

ኢዜማን በመወከል የጉራጌ ዞን ላይ የዞን እና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አንተነህ ተስፋዬ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በሰጡት ምላሽ  የጉራጌ ክልነት ጥያቄ በተዘዋዋሪነት መልሰዋል ሲሉ «የቤትስራ ሰተናቸዋል በህግ አግባብ ምላሽ ያገኛል ብለዋል የፈለገ ቢሆን ክላስተር የሚለው ነገር ድጋሚ ወደ ምክር ቤት አይመጣም » የህብረተሰቡ ጥያቄ በዚሁ ከቀጠለ መልስ የማግና አንዱ መንገድ ነው ብለዋል «አይሆንም አላሉም በቀጥታ በክልል መደራጀት የሚለውን ጥያቄ ማንቀሳቀስእንደሚቻል ጠቋሚ የሆነ ንግግር አድርገዋል »ብለዋል

 እኔ የቤት ስራ እንደመስጠት ነው ማስበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህግ አግባብ ምላሽ ያገኛል ብለዋል። በህግ አግባብ ማለት የፈለገ ቢሆን ክላስተር የሚለው ነገር እንደገና ወደ ምክር ቤት መቶ በክላስተርነት የሚዘጋ

 የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ከክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዘ በተለያዩ ግዜያት ከቤት ያለመቀመጥ አድማ ማድረጉ ይታወሳል በዚሁ በክልልነት ጥያቄ በተመለከተ ተሳታፊ የሆኑ ፖለቲከኞች የህግ ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች በእስር ላይ ይገናሉ።

ማኅሌት ፋሲል 

ዩሃንስ ገብረ እግዚያብሔር