1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ መግለጫ

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 30 2016

በጉራጌ ዞን ከአምስት በላይ «ቋሚ የፀጥታ ኃይል ስምሪት የሚፈልጉ» የግጭት ሥጋት ያንዣበበባቸው አካባቢዎች ተፈጥረዋል ሲል ጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባለው ዋና ጽ/ቤቱ በሰጠው አመግለጫ ዐሳወቀ ።

https://p.dw.com/p/4kJyR
Äthiopien | Gogot Partei
ምስል Solomon Muchie/DW

በርካቶች ሕይወት፣ አካላቸውና ንብረታቸውን እየተነጠቁ ይገኛል

በጉራጌ ዞን ከአምስት በላይ «ቋሚ የፀጥታ ኃይል ስምሪት የሚፈልጉ» የግጭት ሥጋት ያንዣበበባቸው አካባቢዎች ተፈጥረዋል ሲል ጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባለው ዋና ጽ/ቤቱ በሰጠው አመግለጫ ዐሳወቀ ። እነዚህ አካባቢዎች ተከታታይነት ባለው የፀጥታ ሥጋት ውስጥ ከመሆናቸው ባለፈ በፀጥታ መናጋት ብዙ ንፁሐን ዜጎቸ ሕይወታቸው እየተቀጠፈ ይገኛል፣ በርካቶችም ለመፈናቀል ተገደዋል ብሏል ። ወልቂጤ ከተማ ውስጥ «ሥርዓት አልበኝነት ነግሷል» የሚለው ጎጎት ፓርቲ «ድንበር ዘልል» ያላቸው ጥቃቶች በመኖራቸው መንግሥት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል ።

የመግለጫው ዝርዝር ምን ይዟል?

የጉራጌ አካባቢ በቅርብ ጊዜ ታሪክ "በዚህ ልክ በፀጥታ ሥጋት እና ድንበር ዘለል ጥቃቶች የተፈተነበት ጊዜ ያለ አይመስልም" የሚለው ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ "ለዓመታት ሰላማዊ ቀጣና ሆኖ በኖረው አካባቢ አሁን ላይ ከ5 በላይ ቋሚ የፀጥታ ኃይል ስምሪት የሚፈልጉ የግጭት ሥጋት ያንዣበበባቸው አካባቢዎች ተፈጥረዋል" ብሏል በመግለጫው። መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጀሚል ሳኒ በዞኑ ደረሰ ያሉትን ጉዳት ዘርዝረዋል።

«በኢንሴኖ ዙሪያ ያለው ችግር ከ5 ዓመታት በላይ መፍትሔ ሳያገኝ አሁንም በአሰቃቂ ሁኔታ የንጹሐን ሕይወት እየተቀጠፈ ነው። እርቅ ተፈፅሟል በተባለበት ማግስት በርካቶች ሕይወት፣ አካላቸውና ንብረታቸውን እየተነጠቁ ይገኛል። በዚሁ አካባቢ ከመጋቢት 21 እስከ ነሐሴ 26 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ህጻናትና ጨምሮ 32 ወንዶችና 12 ሴቶች በጠቅላላው 44 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ6000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ከ36 ሰዎች በእሥር ላይ ይገኛሉ»፡፡

ኃላፊው በአካባቢው ይፈፀማል ያሉትን ግድያ የፈፀመው ማን ነው የሚለውን ተጠይቀው ያንን መንግሥት መግለጽ እንዳለበት የመለሱ ሲሆን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሰሞኑን እንዳለው ለችግሩ የሸኔ እና የፋኖ እጅ አለበት ማለቱ ይታወቃል። በተጨማሪም የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም ተሳትፎ አድርገዌል የተባሉት ሁሉ እየተያዙ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።

ቆስየ የተባለው አካባቢ ሌላው በጉራጌ ውስጥ "ሙሉ ለሙሉ መንግሥታዊ መዋቅሩ ፈርሶ በጎበዝ አለቆች እጅ የገባ ነው" ያለው ጎጌት ላለፉት 5 አመታት ከጉራጌ ዞኑ ቁጥጥር ውጪ በሌሎች አካላት ቁጥጥር ሥር ይገኛል" ሲልም ገልጿል።

በጉራጌ ዞን  ከ5 በላይ «ቋሚ የፀጥታ ኃይል ስምሪት የሚፈልጉ» የግጭት ሥጋት ያንዣበበባቸው አካባቢዎች ተፈጥረዋል ሲል ጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባለው ዋና ጽ/ቤቱ በሰጠው አመግለጫ ዐሳወቀ ።
በጉራጌ ዞን  ከ5 በላይ «ቋሚ የፀጥታ ኃይል ስምሪት የሚፈልጉ» የግጭት ሥጋት ያንዣበበባቸው አካባቢዎች ተፈጥረዋል ሲል ጎጎት፤ ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባለው ዋና ጽ/ቤቱ በሰጠው አመግለጫ ዐሳወቀ ። ምስል Shewangzaw Wegayehu/DW

"ሙሉ መንግስታዊ አገልግሎት ከመቋረጡ የተነሳ አካባቢው በጎበዝ አለቆች እጅ በመውደቁ የአካባቢው ነዋሪ ለከፋ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋልጧል። ነባር የገበያ ቀኖች ሳይቀር ተቋርጠዋል። ግብር የሚሰበስበውም ከዞኑ ውጭ ያለ አካል ነው"።

በወልቂጤ ከተማ ያለው ችግርም የከፋ መሆኑን የሚገልፀው ጎጎት በከተማው የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የመሳሪያ ግምጃ ቤት ላይ የተፈፀመውን ዝርፊያ በማሳያነት ጠቅሷል።

ችግሩም ከመቆም ይልቅ አድማሱን እያሰፋ የሚደርሰው ጥፋትም በዚያው ልክ እየጨመረ ይገኛል ሲልም በመግለጫው አብራርቷል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ