የጌድኦ ምሁራን ተቃውሞ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2012ማስታወቂያ
ሲዳማ በክልል ከተደራጀ በኋላ ከደቡብ ክልል የሚዋሰነው ድንበር ባለመኖሩ ተነጥሎ የቀረው የጌድኦ ዞን አደረጃጀት በተለያየ ሁኔታ ሊታይ ይገባል ሲሉ የብሄሩ ምሁራን ጠየቁ።ሰሞኑን በዲላ ከተማ የመከሩት እነኚሁ ምሁራን ጌድኦ በልዩ ዞን ይደራጃል በሚል በፌደራል መንግሥት አጥኚዎች የቀረበው ምክረ ሃሳብ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የሌለው የዞኑን መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥን ያላገናዘበ ነው ሲሉ ተቃውመውታል። ምሁራኑ በዚሁ ውይይታቸው ላይ አሁን ያለውን የደቡብ ክልል በ4 ወይም በ5 ቦታዎች በማዋቀር በፊት ወደ ነበረበት አደረጃጀት ይመለስ ቢባል እንኳን በቅድሚያ የሃገሪቱን ሕገ መንግሥት ማሻሻል ይጠይቃል ብለዋል።ውይይቱን የተከታተለው የሃዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዝርዝር ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ