1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን የሲቪል መከላከያን የማጠናከር እቅድ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2018

የጀርመን የሲቪል መከላከያን የማጠናከር እቅድ

https://p.dw.com/p/5EME5
Deutschland Bonn | Bundesamt für Bevölkerungsschutz und Katastrophenhilfe (BBK)
ምስል፦ Christoph Hardt/Future Image/imago images

የጀርመን የሲቪል መከላከያን የማጠናከር እቅድ

የጀርመን መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ለህዝቡ የተሻለ ጥበቃ ለማድረግ 10 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ለማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል። ጥበቃው በሀገር ውስጥ ከሚከሰትም ሆነ ከውጭ ሊሰነዘር ከሚችል አደጋ ህዝቡን መታደግን መሆኑም ተገልጿል። በዚህ ዓመት በመስከረም ወር ነበር የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንት ለሲቪሎች የሚደረግ ጥበቃንና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስተዳደር አቅም እንዲጠናከር እንደሚፈልጉ ያሳወቁት። የዶቼቬለው ማርሴል ፍሩስትናው እንደዘገበው የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንድት የሲቪል መከላከያን ማጠናከር ያስፈለገበትን ምክንያት ለቀውሶች፣ ለአደጋዎች እና ለግጭቶች ቀድሞ ለመዘጋጀት መሆኑን ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ይህ የፖለቲካ ግዴታችንም ነውም ብለዋል። 

በጀርመን የሲቪል ጥበቃ አስፈላጊነት 

 
"የውስጥ እና የውጭ ደህንነት በማይነጣጠል ሁኔታ የተሳሰሩ መሆናቸውን ሁላችንም እንስማማለን። ለዚህም ነው ይህንን ውል ለሲቪል ጥበቃ አቅጣጫ፣ ጽናትና ግብዓቶችን ለማቅረብ መጠቀም በጣም አስፈላጊ የሆነው። ለቀውሶች፣ ለአደጋዎች እና ለግጭቶች እየተዘጋጀን ነው። ለእኛ፣ ለአገራችን ስጋት እየጨመረ በሄደ ቁጥር በአገራችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች በተሻለ ሁኔታ መጠበቅ የፖለቲካ ግዴታ ነው። ይህንንም በሲቪል ጥበቃ ስምምነት ማሳካት እንችላለን።"
ህዝብን ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋዎች የመጠበቅ ተልዕኮ ያለው የሲቪል መከላከያ ለጀርመን አዲስ አይደለም ። ይሁንና በተለይ በጀርመን ከቀዝቃዛው ጦርነት በፊት ይሰጠው የነበረው ትኩረት  ከዚያ በኋላ መቀዛቀዙ አሁን ጀርመን ለየሚያሰጓት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች መቋቋሚያ በቂ ሆነው አለመገኘት ለአሁኑ ዝግጅት ምክንያት መሆኑን  ዶቼቬለ የጠየቃቸው  የኤኮኖሚ ምሁርና የአስተዳደር ባለሞያ ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ተናግረዋል። 
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዶብሪንድት እንዳሉት  10 ቢሊዮን ዩሮው ማለትም (11.6 ቢሊዮን ዶላር) ስራ ላይ የሚውለው በጎርጎሮሳዊው 2029 ዓም ነው። በባለፈው ሳምንቱ መግለጫ ገንዘቡ ለምን ዓላማ ምን  ላይ እንደሚውልም ተናግረው ነበር
"ይህ ከ1,000 በላይ ልዩ ተሽከርካሪዎችን መግዛት እና ለጅምላ ጉዳት ክስተቶች መድረስ የሚችል የሕክምና ግብረ ኃይል ማቋቋምን ያካትታል።ለኬሚካዊ ወይም ባዮሎጂካዊ ክስተቶች አስፈላጊ የሆኑ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዘመናዊ የመከላከያ ልብሶችን ያካትታል። እንዲሁም ለፌዴራል የቴክኒክ እፎይታ ኤጀንሲ (THW)፣ ማዘመኛ መርኃ ግብር ሦስት ቢሊዮን ዩሮ በሪል እስቴት በግንባታ እና በባሉት መሠረተ ልማቶች ላይ በመወረት ሠራተኞችንን እና ቴክኖሎጂን ማዘመን ማስቻል ነው።"

ህዝብን ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋዎች የመጠበቅ ተልዕኮ ያለው የሲቪል መከላከያ ለጀርመን አዲስ አይደለም ። ይሁንና በተለይ በጀርመን ከቀዝቃዛው ጦርነት በፊት ይሰጠው የነበረው ትኩረት  ከዚያ በኋላ መቀዛቀዙ አሁን ጀርመን ለየሚያሰጓት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች መቋቋሚያ በቂ ሆነው አለመገኘት ለአሁኑ ዝግጅት ምክንያት መሆኑን
ህዝብን ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋዎች የመጠበቅ ተልዕኮ ያለው የሲቪል መከላከያ ለጀርመን አዲስ አይደለም ። ይሁንና በተለይ በጀርመን ከቀዝቃዛው ጦርነት በፊት ይሰጠው የነበረው ትኩረት  ከዚያ በኋላ መቀዛቀዙ አሁን ጀርመን ለየሚያሰጓት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች መቋቋሚያ በቂ ሆነው አለመገኘት ለአሁኑ ዝግጅት ምክንያት መሆኑን ምስል፦ Metodi Popow/IMAGO


በመግለጫው መሰረት፣ በመላው ጀርመን ለመጠነ ሰፊ ድንገተኛ ጉዳት የሚያስፈልጉ ከ50 በላይ ቦታዎች ይዘጋጃሉ።ይህ ፅንሰ-ሀሳብ ከጎርጎሮሳዊው ከ2007 ዓም ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ከዚያን ወዲህ ብዙ ተሻሽሏል።  በጀርመን የሲቪል መከላከያ ዋነኛ የፖለቲካ አጀንዳ የሆነው በየካቲት 2022 ዓ.ም. ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በኃላ ነው። ከዚያ በፊት የዛሬ አምስት ዓመት በጀርመን በተለይ በዋነኛነት በራይንላድ ፋልስ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር በደረሰው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ  135 ሰዎች በጎረቤት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ደግሞ የ47 ሰዎች ኅይወት የማለፉ ምክንያት ፣የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ስርዓት አለመስራቱን የማስጠንቀቂያ ድምጽ አለመኖሩ እንደሆነ በወቅቱ መታወቁ ፣የሲቪል መከላከያ እንዲጠናከር ያደረገ ሌላው ሰበብ ነው። ከ35 ዓመታት በላይ ጀርመን የኖሩት ዶክተር ፀጋዬ አሁን ይዘምናል በተባለው የሲቪል መከላከያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የትኛዎቹ እንደሆኑም አንስተዋል።

ሰዎች ከቦምብ ጥቃት ራሳቸውን ሊጠብቁ የሚችሉት እንዴት ነው?

ለሲቪል መከላከያ አስፈላጊ ለሆኑ ውረታዎች ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል።  እንደ ፍሩስትናው ዘገባ ከሆነ ምክንያቱ በመላ ጀርመን ለሲቪል መከላከያ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ-ልማት እጥረት አለ ። ለብዙ አሥርት ዓመታት ሰላም በሰፈነባት በጀርመን ህዝቡ ከውስጥም ይሁን ከውጭ ሊመጣ ስለሚችል  አደጋ ብዙም ልምድ አልነበረውም። ይህም ቸልተኛ እንዳደረገው ይገለፃል ።አይበልና ጀርመን በአንድ ጦርነት ውስጥ ተካፋይ ብትሆን ህዝቡ ከሚጣሉ ቦምቦች እንዴት ራሱን ሊያድን የሚችለው የሚል ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም። 

የጀርመን ህዝብ ቁጥር 84 ሚሊዮን ሲሆን አሁን ያሉት መጠለያዎቹ ግን 478 ሺህ ሰዎች ብቻ ነው መያዝ የሚችሉት።የጀርመን የሲቪል ጥበቃ እና የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ መስሪያ ቤት እንደሚለው ከህዝቡ 0.56 በመቶው ብቻ ነው መጠለያውን መጠቀም የሚችለው። 
የጀርመን ህዝብ ቁጥር 84 ሚሊዮን ሲሆን አሁን ያሉት መጠለያዎቹ ግን 478 ሺህ ሰዎች ብቻ ነው መያዝ የሚችሉት።የጀርመን የሲቪል ጥበቃ እና የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ መስሪያ ቤት እንደሚለው ከህዝቡ 0.56 በመቶው ብቻ ነው መጠለያውን መጠቀም የሚችለው። ምስል፦ Papsch/IMAGO


ጉዳዩ ያሳሰበው 14 ሺህ የየአካባቢውን ባለሥልጣናትን የሚወክለው የጀርመን የከተማችና ማዘጋጃ ቤቶች ማኅበር ከሁለት ዓመት በፊት ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ የፌደራል  መንግሥትን ተማጽኖ ነበር።በማኅበሩ አመለካከት ለሲቪል መከላከያ የ10 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ መታቀዱ ቢያንስ    
በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ወደ 600 የሚጠጉ ግን የወደቁ ከምድር በታች የሚገኙ መጠለያዎችን እንደገና ለማደስ ይረዳል።
ይሁንናየጀርመን ህዝብ ቁጥር 84 ሚሊዮን ሲሆን አሁን ያሉት መጠለያዎቹ ግን 478 ሺህ ሰዎች ብቻ ነው መያዝ የሚችሉት።የጀርመን የሲቪል ጥበቃ እና የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ መስሪያ ቤት እንደሚለው ከህዝቡ 0.56 በመቶው ብቻ ነው መጠለያውን መጠቀም የሚችለው። 

በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀ መመሪያ 

ያም ሆኖ የፌደራል ባለሥልጣኑ ሰዎች ራሳቸውን እንዴት ከአደጋ መከላከል እንደሚችሉ አጠቃላይ መረጃ የሚሰጥ መመሪያ በድረ ገጽ አውጥቷል። በዚሁ «ከቀውሶች እና አደጋዎች በፊት ማቀድ» በሚል ርዕስ በተጻፈው መረጃ ለአስቸኳይ ጊዜ ተዘጋጅተው መቀመጥ ያለባቸው ነገሮች ተዘርዝረዋል።መሠረታዊው ሕግ  ሁሉም ቤቶች ከተቻለ ለ10 ቀናት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያስቀምጡ ይመክራል። 
በጀርመንኛ በእንግሊዘኛ በፈረንሳይኛ በፖላንድ በሩስያ በስፓኝ በቱርክና በዩክሬን ቋንቋዎች የተdfጻፈው ይኽው መመሪያ  ለአስቸኳይ ጊዜ ከሚያስፈልጉት ውስጥ ውሐና ምግብ መድኃኒቶች እና መጸዳጃዎችን መያዛቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ