1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ቅኝ ግዛት እና የአፍሪቃውያን እልቂት

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

የራይንሽ ተልዕኮ ቤተክርስትያን የተባለችው የጀርመን ቤተክርስታያን ከሄሬሮ ህዝቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጥራ እንደነበር ይነገርላታል። ጀርመኖቹ በኦካሃንጃ፣ ኦትጂምቢንግዌ እና በዊንድሆክ በስምምነት አብረው መኖር የጀመሩበት አጋጣሚም ነበር ። በዚህም በርካታ ሄሬሮዎችም ወደ ክርስትና እምነት እንዲመጡ መንገድ ከፍቶላቸዋል።

https://p.dw.com/p/4ddFy
Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል DW

የራይንሽ ተልዕኮ ቤተክርስትያን የተባለችው የጀርመን ቤተክርስታያን ከሄሬሮ ህዝቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጥራ እንደነበር ይነገርላታል። ጀርመኖቹ በኦካሃንጃ፣ ኦትጂምቢንግዌ እና በዊንድሆክ በስምምነት አብረው መኖር የጀመሩበት አጋጣሚም ነበር ። በዚህም በርካታ ሄሬሮዎችም  ወደ ክርስትና እምነት እንዲመጡ መንገድ ከፍቶላቸዋል።

የራይንሽ ተልዕኮ ቤተክርስትያን የተባለችው የጀርመን ቤተክርስታያን ከሄሬሮ ህዝቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጥራ ነበር።  ጀርመኖቹ በኦካሃንጃ፣ ኦትጂምቢንግዌ እና በዊንድሆክ በስምምነት አብረው መኖር የጀመሩበት አጋጣሚም ነበር ። በዚህም በርካታ ሄሬሮዎችም ወደ ክርስትና እምነት እንዲመጡ መንገድ ከፍቶላቸዋል። 

የጀርመን ቅኝ ገዥ አስተዳደር በገባ ጊዜ  ከጎሳዎቹ ጋር የጥበቃ ስምምነት ብለው የሚጠሩት አይነት ስምምነት ነበራቸው። ልብ መባል ያለበት ነገር ግን በወቅቱ  በናማ እና በሄሬሮ ጎሳዎች መካከል በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንደነበረ ነው።

በሁለቱም በኩል አንዱ አንዱን ይወርሩ እንደነበር ነው የሚነገረው

በዚህም ምክንያት ሄሬሮዎች  ከናማዎች እንዲከላከሉላቸው ከጀርመኖች ጋር  የጥበቃ ስምምነት ነበራቸው። በተመሳሳይ ናማዎችም እንዲሁ ከጀርመኖች ጋር  የጥበቃ ስምምነት ነበራቸው። 

ነገር ግን እነዚህ ስምምነቶች ሁለቱንም አልጠቀሟቸውም።  አስገራሚው ነገር ግን  ናማዎች በሄሬሮዎች ላይ እንዲሁም ሄሬሮዎች በናማዎች ላይ ስጋት አልነበሩም ።  በዋነኛነት በሄሬሮዎች ላይ የተፈፀመው የመሬት ወረራ ግን የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት  እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል።

በእርግጥ ያ የሁነቱ  አንዱ ገጽታ ነበር።  በ1897 የቀንድ ከብቶችን የሚያጠቃው ወረርሽኝ ለሄሬሮዎች  ዋና ሀብት የነበረውን አ,ጠቃላይ የእንስሳት እርባታ ማጥፋቱን ታሪክ ጽፎታል።   በ 1903 ቁጥራቸው ከ 5,000 ብዙም የማይበልጡ   ጀርመናውያን ቅኝ በያዙት ግዛት ውስጥ ይኖሩ ነበር። ጀርመኖቹ በሂደት  ለእርሻ የሚሆን ሰፊ መሬት የግድ አስፈላጊያቸው መሆን ጀመረ ። እንደ ፕሮፌሰር ብሪጊት ራይንዋልድ ገለጻ፣ ለዚህ ሲባል ምንም እንኳ ስምምነቶችን የጣሰ ቢሆንም  የቅኝ ገዥ ባለ ሥልጣናት  ሄሬሮዎችን ከነከብቶቻቸው ከመሬቱ ላይ ለማንሳት አዲስ ውጥን ወጠኑ ።

ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ እጅግ የተገደቡ የብድር ሕጎች፣ በመጨረሻም የአገሬው ተወላጆችን  ወደ  ሌላ ቦታ የመወሰ,ድ ግዴታ የሚጥሉ   ዕቅዶች  ጦርነት ቀስቃሽ ነበሩ።

ሄሬሮዎች ንብረታቸው ከመወረስ ፣ መደፈር እና ከሚደርስባቸው አካላዊ ቅጣት በተጨማሪ  አሁን ጀርመኖች በባለቤትነት በያዟቸው መሬቶች ላይ ተገደው የጉልበት ስራ እንዲሰሩ መደረጉ ውጥረቱን የበለጠ እንዳባባሰው የሚናገሩት ደግሞ ካቲጂዋ ናቸው።

ሄሬሮዎችን ያታለላቸው የመጨረሻው ክስተት ከአለቆቻቸው አንዱ የነበረው የዘካሪያ ቤራዋ ሴት ልጅ መደፈር ነበር ። 

የዲትሪች ጉዳይ እንደሚታወቀው አንድ ጀርመናዊ ነጋዴ ላለመደፈር ስትታገል የነበረችን ሴት ከደፈራት በኋላ ሲገድላት መመልከቱ ያመጣበት ጣጣ ነው።  በወንጀል ፈጻሚው ላይ የነፍስ ግድያ ወንጀል ክስ ቢመሰረትበትም ፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ "ጊዜያዊ እብደት” ያመጣበት ችግር  ነው ሲል ከወንጀሉ  ነፃ አወጣው። ከዚያ በኋላ በነበረው የፍርድ ሂደት ዲትሪች እንዲታሰር መደረጉን ተከትሎ  ጉዳዩ በአገሬው ተወላጆች ላይ ቁጣ ቀስቅሷል። እናም ህጎቹ  ለጀርመናውያን እና ለአካባቢው ነዋሪዎች እኩል መብት እንደሌላቸው በብዙ መልኩ ያሳየ ነበር ።

በ1904 መጀመሪያ ላይ የሄሬሮ አርበኞች ከ100 በላይ የጀርመን ሰፋሪዎችን ገደሉ ። ለዚህ ደግሞ በተለይ ጥቁሮቹ ስልጡን ጀርመናዊ ነን ከሚሉት ያነሱ ናቸው የሚለው የዘረኝነት አስተሳሰብ የራሱን አስተዋጽዖ አበርክቷል። ።  ካይዘር ዊልሄልምን ጨምሮ በአመጹ የተበሳጩ  የጀርመን መሪዎች ሄሬሮዎችን የማጥፋት ጥያቄ አንስተዋል።  በዚህም የሄሬሮ መሪዎች ያስነሱትን አመጽ እና ግድያ  ለመቆጣጠር ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከበርሊን አስደንጋጭ መልዕክት ተላከ።

በጎርጎርሳውያኑ 1904 አጋማሽ ላይ ጄኔራል ሎታር ቮን ትሮታ በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ አዛዥ ሆኖ ሲሾም  በሺዎች የሚቆጠሩ የጀርመን ወታደሮች  ወደ ቅኝ ግዛቱ ተላኩ። ቮን ትሮታ ሄሬሮዎችን ማሸነፍ አልነበረም ፍላጎቱ ይልቁኑ በእርሱ አባባል  እነርሱን ለማጥፋት ነበር ቆርጦ የተነሳው። በዚህም በደንብ የታጠቁ ወታደሮቹ የሄሬሮ ተዋጊዎችን ዋተርበርግ ላይ በፍጥነት ከበባ በማድረግ የሄሬሮዎችን የመዋጋት አቅም መስበር ቻሉ።

«ጀርመኖች በጄኔራላቸው ሎተር ቮን ትሮታ አማካኝነት ሄሬሮዎችን በሌላ መንገድ እንደሚያጠፉአቸው  ስላረጋገጡ በመጀመሪያ ማድረግ የነበረባቸው የውሃ ጉድጓዶች እንዲመረዙ የሚያደርጉ ትዕዛዞችን  አስተላልፈዋል። »

በጀርመን ግዛት ውስጥ የተገኘ ማንኛውም ሄሬሮ እንዲገደል የመጨረሻ ትዕዛዝ ተላለፈ። ሄሬሮዎች ወደ ቦትስዋና ወደተዘረጋው እና ኦማሄኬ ወደ ተባለ  በረሃማ አካባቢም ተባረሩ ።

«ሄሬሮዎች ወደ ሻርክ ደሴት እና ስዋኮፕመንድ የማጎሪያ ካምፖች ተጋዙ ። እናም ስለሄሬሮዎች እልቂት የሚወሳ ከሆነ በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ፣ የውሃ ጉድጓዶችን በመመረዝ እና በካልሃሪ በረሃ በረሃብ እና የውሃ ጥም እንዲያልቁ መደረጋቸው በዋነናነት ተጠቃሾች ናቸው።»

ትክክለኛውን አኃዝ መግለጽ ባይቻልም በዘር ፍጅቱ እስከ 80 000 የሚደርሱ የሄሬሮ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት እንዳለቁ ይገመታል። በወቅቱ በባህር ዳርቻዎች በነበሩ ማጎሪያ ካምፖች  ረሃብ እና  ጥምን ጨምሮ ፤ በሚፈጸምባቸው ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ ፣ ብርድ 75 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። ሌሎች ከ10 እስከ 20 ሺ የሚገመቱ የናማ ጎሳ አባላትም እንዲሁ በዚሁ የጀርመን ቅኝ ግዛት አስተዳደር ወቅት ተገድለዋል። ከጀርመኖቹ ወገን የተገደሉት ሰዎች በንጽጽር አነስተኛ ሲሆኑ እስከ አንድ ሺ የሚጠጉ ጀርመናውያን እንደተገደሉ ይገመታል።

በወቅቱ እንደ አለቃ ሳሙኤል ማሃሄሮ ያሉ ጥቂት ሰዎች ማምለጥ ችለው ነበር ።  ነገር ግን የሄሬሮ እና የናማ ህዝቦች በደቡባዊ አፍሪካ ውስጥ ሲበታተኑ  በጀርመን ቅኝ ግዛት ውስጥ የቀሩት ጥቂቶች ደግሞ ጀርመኖቹ በባለቤትነት በያዟቸው  ከተሞች እና መሬት ላይ ተገደው የጉልበት ሥራ  የመስራት ዕጣ ፈንታ ገጥሟቸዋል።  ከ100 ዓመታት በኋላም አብዛኛው መሬት አሁንም ድረስ በጀርመን ዝርያ ናሚቢያውያን  እጅ ይገኛል።

በጎርጎርሳውያኑ 2021 ይፋ በተደረገው  የሁለትዮሽ የጋራ መግለጫ ጀርመን ለናሚቢያ መንግስት ለ 30 ዓመታት የሚሰጥ የ1.1 ቢሊዮን ዩሮ ቃል ገብቷል ።

ቢሆንም ይላሉ ዶ/ር ሄኒንች ሜልበር

«የጀርመን መንግስት ከዚህ ዘመን አንፃር የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ብሏል፤  ይህ ማለት ግን  በጣም አስፈላጊ የሆነ  የህግ ማስጠንቀቂያ የሚያስነሳ ነው።  ምክንያቱም በሌላ አባባል በወቅቱ የተፈጸመው  የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም እንደማለት ነው። ወይም ደግሞ የዘር ማጥፋት ስለመሆኑ ተስማምቶ መቀበልን  በተመለከተ ምንም አይነት ህጋዊ አንድምታ የለም እንደማለት ነው። »

የሄሬሮ እና የናማ መሪዎች በወሳኝ መልኩ በጉዳዩ ላይ በጭራሽ እንዳልተማከሩ አልያም በቀጥታ በድርድሩ ውስጥ እንዳልተሳተፉ ነው ምሁሩ የሚገልጹት። በጥር 2023 የናማ እና የሄሬሮ ማህበረሰቦች ጠበቆች የጀርመን እና የናሚቢያ የጋራ መግለጫ የናሚቢያን ህገ መንግስት የተለያዩ አንቀጾችን የሚጻረር እና ልክ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል።

እንደ አስተዳዳሪው ካትጂዋ፣ ጀርመን ከተጎዱ ወገኖች ይቅርታን መጠየቅ ሳይሆን ከናሚቢያ መንግስት ጋር መነጋገርን መርጣለችና ምንም ይሁን ምን ከታሪክ አንጻር ተቀባይነት የሌለው ነው።

«ለዚህ ነው ሄሬሮዎች እና ናማዎች አሁንም ድረስ የዘር ማጥፋት ፈጽመሃል እያሉ ያሉት ፤ ካሳ መክፈል አለብህ ፤ ምን ያህል መክፈል እንዳለብህ የምንወስን ደግሞ እኛ ነን ።»

«ጀርመን ከ23 የአይሁድ ማህበረሰቦች ጋር ተደራድራለች። በተጨማሪም፣ ከእስራኤል መንግስት ጋር ፤ የአይሁድ ማኅበረሰብ የሚፈልገውን፣ የጠየቀውን እንዲሁም  የእስራኤል መንግሥትም የሚፈልገውን አገኘ። የናሚቢያ መንግስት ወይም ግዛቱ የተወሰነ የዋስትና ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ ለዚህም መደራደር ይችላሉ እያልን ነው። ነገር ግን ሄሬሮዎች እና ናማዎች የተለየ ጉዳት ነው የደረሰባቸው ።»

እናም ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ፣ ምንም እንኳን የቅኝ ግዛት ካለፈ ክፍለዘመን ቢያስቆጥርም ፣ ደቡብ አፍሪካዊ ወረራ እና አፓርታይድ ቢያልፍም ፤ በመጨረሻ በ 1990 ነፃነታቸውን ቢጎናጸፉም የሄሬሮ እና የናማ ህዝቦች ግን  ቅድመ አያቶቻቸውን ፈጽሞ አይዘነጉም ፣

ሄሬሮዎች ግልጽ የሆነ አፈ ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ናቸው።   በናሚቢያ ውስጥ የነበሩ ሁሉም የእርሻ ቦታዎች የሄሬሮ እርሻዎች ነበሩ። , አሁንም ድረስ የሄሬሮ ስሞች ነው ያሏቸው ። እና እነዚያ ስሞች ደግሞ  በእርሻው ውስጥ አልያም ወይም መሬት ላይ የተቀበረውን የመጀመሪያውን ሄሬሮ ያመለክታሉ ማለት ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰው የሚናፍቁት ቤተሰባቸው የት እንዳሉ እና ስረ መሰረታቸውን ያውቃሉ።