የድምጻዊ ወንድዬ አበበ የሙዚቃ ሕይወት እና ስራዎች | ኢትዮጵያ | DW | 28.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የድምጻዊ ወንድዬ አበበ የሙዚቃ ሕይወት እና ስራዎች

ትውልድ እና እድገቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ፤ በአሁኑ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን እንደሆነ ይናገራል። የሙዚቃ ስራን ገና በለጋ እድሜው በተቀላቀለበት የወታደር ቤት መጀመሩን ይናገራል፤ ድምጻዊ ወንድዬ አበበ ወይም በቅጽል ስሙ ወንድዬ ኮንታ ። የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ነው።

የድምጻዊ ወንድዬ አበበ የሙዚቃ ሕይወት እና ስራዎች

ትውልድ እና እድገቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ፤ በአሁኑ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን እንደሆነ ይናገራል። የሙዚቃ ስራን ገና በለጋ እድሜው በተቀላቀለበት የወታደር ቤት መጀመሩን ይናገራል፤ ድምጻዊ ወንድዬ አበበ ወይም በቅጽል ስሙ ወንድዬ ኮንታ ። በዜማ የትውልድ አካባቢውን በማስተዋወቅ የሚታወቀው ወንድዬ አበበ ገና በወታደር ቤት ሳለ በአብዛኞቹ ዘንድ ብዙም የማትታወቀውን ትንሺቷን ልዩ ወረዳ ቆርጦ መነሳቱን ይናገራል። ስለኮንታ ተናግሮ አይጨርስም ።

በተመሳሳይ ጊዜ የእግር ኳስ ተጫዋች እና ሙዚቀና መሆኑን እህል ውኃውን ለመለየት እስኪያዳግተው ተፈታትነውታል። ሙዚቃው አሸንፎት እጁን እስኪሰጥ ድረስ በተለይ በወታደር ቤት በነበረው ቆይታ በተለያዩ የጦሩ መዋቅር ውስጥ ከዚያም ከውትድርና ከተሰሰናበተ በኋላ እስከፕሪምየር ሊግ የደረሰ የእግር ኳስ ተጫዋች እንደነበር የሚናገረው ወንድዬ ወደፊት በሙዚቃ ስራው የትውልድ አካባቢውን የማስተዋወቅ ህልም እንዳለው በድፍረት ይናገር እንደነበር  ይገልጻል ። ሹሩር ጋሼ እና ሎሜ ሎሜ ስራዎቹ በተለይ ድምጻዊ ወንድዬን ከአድማጭ ተመልካቹ ያስተዋወቁ ስራዎቹ ናቸው ።  

በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ክልል የሚገኙ አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች በጥምረት ያዘጋጁት የህዳሴው ግድብ ሙዚቃ ወይም ዋሴ ዋሴ በድምጽ ከመሳተፍ እስከማስተባበር የደረሰ ተሳትፎም ነበረው ። ይህ ተሳትፎው የኢትዮጵያ የባህል ሙዘቀኞች ቡድንን ወክሎ በጎርጎርሳውያኑ 2019 በናይጄሪያ በተዘጋጀው የባህል ሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ እስከማሸነፍ የደረሰ ተሳትፎ አድርጓል። 

በሙዚቃ ስራዎቹ የትውልድ ስፍራው የሆነችውን ኮንታን ሲያስተዋውቅ እንደ መቆየቱ የጨበራ ጩርጩራ በጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ሀገር አቀፍ የፓርክ ልማት መርኃ ግብር ውስጥ መካከተቱ እርሱ ቀደም ብሎ ለጀመረው አካባቢውን የማስተዋወቅ ስራ እውቅና ያስገኘለት እንደነበር ወንድዬ ይናገራል። 

ድምጻዊ ወንድዬ አበበ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን ከሚያስተዋውቀው ስራው ባሻገር አሁን ላይ ሀገሪቱን በቀደመው የውትድርና ሞያው የማገልገል ፍላጎት እንዳለው ይናገራል። እንግዲህ አድማጮቻችን ለዛሬ ያልነው ዝግጅታችንም በዚሁ ተጠናቋል ሳምንት በሌላ ዝግጅት ዳግም እንጠብቃችኋለን እስከዚያው ሰላም ቆዩን ።

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ

 

Audios and videos on the topic