የዩክሬይን ቀውስ፣ የአውሮጳ ህብረት እና ሩስያ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የዩክሬይን ቀውስ፣ የአውሮጳ ህብረት እና ሩስያ

በአሁኑ ጊዜ ምዕራባውያንን፣ በተለይም ፣ አውሮጳን እያሳሰበ ያለው ፈተናም ውስጥ የጣለው የዩክሬይን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ከሩስያ ጋ የገቡበት እሰጣ ገባ እና የፖለቲካ ፍጥጫ ነው።

ባለፈው መጋቢት ወር ቂ,ዩክሬይንን ግዛት ክሪሚያ ወደ ግዛቷ ካጠቃለለች እና ዓማፅያንም በምሥራቃዊ ዩክሬይን ውጊያ ከከፈቱ ወዲህ ሩስያ ያልተወገዘችበት እና የማዕቀብ ማስጠንቀቂያ ዛቻ ያልቀረበበት የአውሮጳ ህብረት ስብሰባ የለም። ከዚህ ጎንም ባለፈው ሀምሌ 10 በምሥራቅ ዩክሬይን ሲበር ተመቶ የተከሰከሰውa እና የ298 ሰዎች ሕይወት የጠፋበት የማሌሽያ የመንገደኞች ማመላለሺያ አይሮፕላን አደጋ በሩስያ እና በአውሮጳውያኑ መካከል ያለውን ልዩነት እንዳያባብሰው አስግቶዋል። የዩክሬይን ቀውስ፣ የአውሮጳ ህብረት እና የሩስያ የፖለቲካ ፍጥጫ፣ የኤኮኖሚው ማዕቀብ የሚፈጥረው ጫና እና የዩክሬይን መጻዒ ዕድል የዛሬው የአውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic