የዕርቅ ኮሚሽንና የባሕርዳር ነዋሪዎች ዉይይት
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዕርቀ ሠላም ኮሚሽን አባላት በሳምንቱ ማብቂያ ላይ ከባሕርዳር ነዋሪዎችና ከአማራ መስተዳድር ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።በዉይይቱ ወቅት ሥለ ኮሚሽኑ ኃላፊነት፣የስራ ዘመን እና ሥለ ዕርቀ-ሠላም እሳቤ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የኮሚሽኑ አባላት መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።ከአስር ወር በፊት የተመሰረተዉ ብሔራዊ የዕርቀ-ሠላም ኮኮሚሽን ከዚሕ ቀደም ከአዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያና ከትግራይ ነዋሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዉይይት አድርጎ ነበር።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ