1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ መግለጫ ስለጄኔቫ ድጋፍ ማሰባሰብና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2016

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የከፋ የሰብአዊ ቀውስ ድጋፍ ለማሰባሰብ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ውስጥ በተደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ ከታቀደው ዝቅ ያለ ገንዘብ ቃል መገባቱ ተገለጠ ። አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታቅዶ ቃል የተገባው 630 ሚሊዮን ዶላር መሆኑም ተጠቅሷል ።

https://p.dw.com/p/4ew1W
Äthiopien Logo des Außenministeriums

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ዝርዝር ጉዳዮች

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የከፋ የሰብአዊ ቀውስ ድጋፍ ለማሰባሰብ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ውስጥ በተደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ የማሰባሰብሥራ ከታቀደው ዝቅ ያለ ገንዘብ ቃል መገባቱ ተገለጠ ። አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታቅዶ ቃል የተገባው 630 ሚሊዮን ዶላር መሆኑም ተጠቅሷል ። ጄኔቫ ውስጥ መንግስት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተሰበሰበበት አዳራሽ ውስጥ የተገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን መንግሥት በተለይ በአማራዎች ላይ ይፈጽመዋል ያሉትን በደል በመግለጥ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ የሚያሳይ የድምፅ እና ምስል መረጃ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በስፋት ተዛውሯል ። የውጭ ጉዳይ መሥራያ ቤት ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ተደርጎ ስለነበረው የመግባቢያ ሠነድ ስምምነት፤ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ስላሉ የድንበር ማካለል ጉዳዮችም ማብራሪያ ሰጥቷል ።  

የውጭ ጉዳይ መሥራያ ቤት ቃል አቀባይ አቶ ነቢዩ ተድላ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ሥምምነትን በተመለከተ የተጠየቁ ሲሆን "አዲስ ወይም የተቀየረ ነገር የለም" በማለት "የተቀየረ ካለ የምናሳውቅ ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል ።

ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያሉ የድንበር ማካለል ጉዳዮችን አስመልክቶም የሀገራትን ጥቅም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ባመቺ ጊዜ እና ወቅት ላይ ሥራዎችን ለመሥራት ይሞከራል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ መንግሥት በጀመረው ሦስተኛ ዙር ዜጎችን ከመካከለኛው ምሥራቅ የማስመለስ ተግባር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደረጉ 12 በረራዎች 4200 ዜጎችን ማስመለስ መቻሉን ተናግረዋል።

የመግለጫው ዝርዝር ጉዳዮች

በዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ መንግሥት ባለፉት ስድስት ዓመታት አከናወናቸው የተባሉ በጎ ተግባራት የተዘረዘሩ ሲሆን ፣ ድክመቶች ወይም የገጠሙ ችግሮች ግን አልተጠቀሱም። ቃል አቀባዩ መንግሥት በሦስተኛ ዙር ስለጀመረው እና በሕገ ወጥ መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በተለይም ሳውዲ አረቢያ ተጉዘው በፀጥታ ኃይላት ተይዘው በተለያዩ እሥር ቤቶች ውስጥ እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የማስመለስ ሥራ ማብራሪያ ሠጥተዋል። «እስካሁን ባለው ወደ 4200 በላይ ዜጎቻችን ተመልሰዋል ።»

በጄኔቭ የተመድ ጽሕፈት ቤት
በጄኔቭ የተመድ ጽሕፈት ቤትምስል Salvatore Di Nolfi/KEYSTONE/picture alliance

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ድንበርን በተመለከተ ጥያቄ ከጋዜጠኞች ቀርቧል

በኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና በጦርነት ምክንያት ለተከሰተው  ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ይሆን ዘንድ በመንግሥት እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ጄኔቫ ላይ በተደረገው ገንዘብ የማሰባሰብ ሰሞነኛ ጥረት 630 ሚሊዮን ዶላር ቃል መገባቱን የገለፁት ቃል ዐቀባዩ ለማሰባሰብ ታቅዶ ከነበረው 1 ቢሊዮን ዶላር አንፃር ዝቅተኛ መሆኑ ተጠቅሶ ይህ ለምን እንደሆነ ተጠይቀዋል።

 "አይነተኛ አስተዋጽዖ ሊያደርግ የሚችል ድጋፍ ተገኝቷል " ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ስላደረገችው የመግባቢያ ስምምነትም  አዲስ ነገር አለመኖሩ ተገልጿል። ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው የድንበር ማካለል ሥራን በተመለከተም ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቷል። "የሀገራትን ጥቅም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ባመቺ ጊዜ እና ወቅት ላይ ሥራዎችን ለመሥራት ይሞከራል" ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ