1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ መመራቱ እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ገበያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

ድሬደዋን ጨምሮ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በምግብ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች እና ነጋዴዎች ገለፁ ። በድሬደዋ በብረት ዋጋም ላይ እስከ ሁለት መቶ ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ ተገልጿል ።

https://p.dw.com/p/4jVtH
Äthiopien Alltag l Dire Daw Market
ምስል Mesay Teklz/DW

ድሬ ዳዋ ፣ ሐረር እና ጅጅጋ ከምጣኔ ሀብት መሻሻል በኋላ ምን ይመስላሉ?

ድሬደዋን ጨምሮ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በምግብ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች እና ነጋዴዎች ገለፁ ። በድሬደዋ በብረት ዋጋም ላይ እስከ ሁለት መቶ ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ ተገልጿል ።

በአብዛኞቹ አካባቢዎች ከዋጋ ጭማሪው ባለፈ በተለይ እንደ ዘይት ያሉ ምርቶችን በመደበቅ ከገበያ እንዲጠፉ እንደሚደረግ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል። የድሬደዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ገነት አበበ በከተማው የምግብ ዘይትን ጨምሮ መጠኑ ቢለያይም በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

 

አቶ ፋንታሁን የተባሉ ሌላኛው አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው በብረት ዋጋ ላይ እስከ ሁለት መቶ ብር የሚደርስ ጭማሪ መኖሩን ገልፀዋል።

«የኤኮኖሚ ማሻሻያው» የብር አቅም መዳከም ለብዙኀኑ ሕዝብ ምን ማለት ይሆን?

 በቅርቡ በከተማዋ ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ምርት በሚደብቁ እና ዋጋ በሚጨምሩ አካላት ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ገልፀው ነበር። ይሁን እንጂ እርምጃው ያመጣውን ፋይዳ ለመጠየቅ የድሬደዋ ንግድ ቢሮ ባለስልጣናትን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግኩት ጥረት አልተሳካም።

በሌላ በኩል በሀረር በተመሳሳይ መልኩ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ለዶይቼ ቬለ የጠቀሱት አቶ ኪዳኔ የተባሉ  የሀረር ነዋሪ የክልሉ መንግስት የመሸጫ ዋጋ ተመን በማውጣት እየወሰደ ባለው እርምጃ መሻሻሎች መኖራቸውን ገልፀዋል።

የሐረር ከተማየገበያ ስፍራ
በሀረር በተመሳሳይ መልኩ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ለዶይቼ ቬለ የጠቀሱት አቶ ኪዳኔ የተባሉ  የሀረር ነዋሪ የክልሉ መንግስት የመሸጫ ዋጋ ተመን በማውጣት እየወሰደ ባለው እርምጃ መሻሻሎች መኖራቸውን ገልፀዋልምስል Amanuel Sileshi/AFP

 

 

አብዛኞቹ ሸቀጦች በህጋዊ እና ህጋዊ ባልሆነ መልኩ የቅርብ መዳረሻ በሆነችው የሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋም በሸቀጦች ላይ ተመሳሳይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ወ/ሮ መርየም የተባሉ የጅግጅጋ ነዋሪ ነጋዴ ገልፀዋል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት የፖሊሲ አላባዎች የሚሳኩ ናቸው?

መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት በገበያ እንዲመራ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በጅግጅጋ በሸቀጦች ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ለመግታት በሚል በተወሰኑ ሸቀጦች ላይ የጅምላ መሸጫ ዋጋ ተመን አውጥቶ በስራ ማዋሉን አስታውቋል።ይህም መጠነኛ መሻሻል ፈጥሯል ተብሏል።

መጋዘን ውስጥ የተከማቸ ዘይት
መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት በገበያ እንዲመራ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በጅግጅጋ በሸቀጦች ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ለመግታት በሚል በተወሰኑ ሸቀጦች ላይ የጅምላ መሸጫ ዋጋ ተመን አውጥቶ በስራ ማዋሉን አስታውቋል።ምስል Mesay Teklz/DW

በኢትዮጵያ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ መፈቀዱ

ድሬደዋን ጨምሮ በሀረር እና ጅግጅጋ ከተሞች በሸቀጦች ላይ ከታየው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ ባለፈ ምርቶችን ከገበያ የመሰወር ሁኔታ በስፋት እንደነበር የሚገልፁት ሸማቾች ይህ ድርጊት አሁንም በአንዳንድ ምርቶች ላይ እንደሚታይ አስረድተዋል።

በድሬደዋ ሸቀጦች በጅምላ በሚሸጡባቸው የንግድ ቦታዎች እና የሽያጭ መደብሮች በተለይ ዘይት መጥፋቱን ለመታዘብ ችያለሁ።

የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ
ድሬደዋን ጨምሮ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በምግብ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች እና ነጋዴዎች ገልጸዋልምስል Mesay Teklz/DW

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ