የኮንሶና የአሌ ተፈናቃዮች የርዳታ ጥሪ | ኢትዮጵያ | DW | 28.07.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኮንሶና የአሌ ተፈናቃዮች የርዳታ ጥሪ

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ክልል በኮንሶና በአሌ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አንገኛለን አያሉ ነው። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት በግጭቱ ከአካባቢያቸው በመሽሽ በተለያዩ ስፍራዎች ከተጠለሉ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል።

የእህል ጎተራዎቻችን በአሳት በመውደማቸው እስከአሁን የሚላስ የሚቀመስ አላገኘንም

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ክልል በኮንሶና በአሌ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አንገኛለን አያሉ ነው። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት በግጭቱ ከአካባቢያቸው በመሽሽ በተለያዩ ስፍራዎች ከተጠለሉ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። በግጭቱ የመኖሪያ ቤቶቻችንና የእህል ጎተራዎቻችን በአሳት በመውደማቸው እስከአሁን የሚላስ የሚቀመስ አላገኘንም የሚሉት ተፈናቃዮቹ ያለመጠለያ በሜዳ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ አመራሮች ግጭቱን ሸሽተው ወደ አካባቢው የገቡ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለበላይ አካላት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት በበኩላቸው አሁን በስፍራው አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ በመምጣቱ የኮልሜ ክላስተር በተባለው አካባቢ ለተፈናቀሉት ጊዜያዊ የምግብ ድጋፍ ማቅረብ መጀመራቸውን ገልጸዋል ። ተፈናቃዮቹንና የአካባቢውን ባለስልጣናት ያነጋገረው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ተከታዩን ዝርዝር አድርሶናል።

ሸዋንግዛዉ ዉጋየሁ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ   

Audios and videos on the topic