1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሌራ ወረርሽኝ በሐረሪ ክልል 

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2011

እስካሁን  በክልሉ 6 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከመካከላቸውም አንዱ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ነው። በኮሌራ ከተያዙት አብዛኛዎቹ ከኦሮሚያ ክልል ከምሥራቅ ሐረርጌ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3Ntwc
Karte Sodo Ethiopia ENG

«ስድስት የኮሌራ ታማሚዎች ታክመዋል»

በሐረሪ ክልላዊ መስተዳድር የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው ለዶቼቬለ እንደተናገረው እስካሁን  በክልሉ ስድስት ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከመካከላቸውም አንዱ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ነው። በኮሌራ ከተያዙት አብዛኛዎቹ ከኦሮሚያ ክልል ከምሥራቅ ሐረርጌ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል። የበሽታውን ሥርጭት ለመከላከልም የክልሉ ጤና ቢሮ የበኩሉን ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግሯል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ