የኬንያ ፖለቲከኞች ዉዝግብ
ሐሙስ፣ መስከረም 18 2010ማስታወቂያ
የኬንያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች በመጪዉ ጥቅምት አጋማሽ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ዛሬም አልሰከነም።የፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ የጁቢሊ ፓርቲ እና በራይላ ኦዲንጋ የሚመራዉ ናሳ የተባለዉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተወካዮች ዛሬ ሥለምርጫ ለመነጋገር ቢሰሰበሰቡ ስብሰባዉ ባፍታ ተበትኗል።የገዢዉ ፓርቲ የሚበዛበት የሐገሪቱ ምክር ቤት በበኩሉ የሐገሪቱን የምርጫ ሕግ ለመቀየር አዳዲስ ማሻሻዎችን አቅርቧል።የተቃዋሚዉ ፓርቲ የምክር ቤት እንደራሴዎች ማሻሻያዉን በመቃወም የምክር ቤቱን ሥብሰባ ረግጠዉ ወጥተዋል።የናይሮቢ ተባባሪ ዘጋቢያችን ፍቅረ-ማርያም መኮንንን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ፍቅረ-ማርያም መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ