የኬንያ ቴሌቪዥን ያቀረበው ዘጋቢ ፊልም መንግስት ማስከፋቱ
ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2001ማስታወቂያ
የቴሌቩዥን ጣቢያው ከዘጋቢ ፊልሙ ሁለቱን ክፍል ካስተላለፈ በኃላ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጣቢያው ዘገባውን ማስተላለፉን እንዲያቆም ሙከራ ማድረጋቸውን ኔሽን የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል ። የኢትዮጵያ መንግስት ፣ ዘጋቢ ሪፖርቱ መሰረት የሌለው ፕሮፖጋንዳ የሚነዛ ነው ሲል ነው የሚከሰው ። የዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ ድርጅት CPJ በበኩሉ ይህ ተግባር መንግስት ስልጣኑን ላለማጣት ሁሉንም አማራጭ እንደሚጠቀም አመልካች ነው ሲል ወቅሷል ።
አበበ ፈለቀ/ ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ