የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና የጸረ ማፍያ አስተያየት | ዓለም | DW | 24.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና የጸረ ማፍያ አስተያየት

ጣሊያን ዉስጥ በሶስት ክፍላተ ሃገራት በካላብሪያ እንድራንጌታ፣ በሲሲሊ ማፊያ፣ እንዲሁም በካምፓኛ ኔፕልና አካባቢዉ ደግሞ ካሞራ የተባሉ የተደራጁ የአመፅ ቡድኖች መኖራቸዉ የአደባባይ ምስጢር ነዉ።

ቡድኖቹ ኅብረተሰቡን የሚያዉኩ የተለያዩ የአመፅ ድርጊቶችን በመፈጸም ይወቀሳሉ። የዚህ ቡድን አባላት የሆኑ ታዲያ በቤተ ክርስቲያን እየተገኙ እንደሰላማዊዉ ምዕመን የአገልግሎት ተሳታፊ መሆናቸዉ ኅብረተሰቡን እያነጋገረ ቀሳዉስቱንም እያስወቀሰ ነዉ። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ገደማ በደቡባዊ ጣሊያን አንደኛዉ የአመፅ ቡድን ማለትም እንድራንጌታ ይንቀሳቀስበታል በሚባለዉ ካላብሪያ ግዛት ለአንድ ቀን በመገኘት መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። በእዚያም 90ሺህ ህዝብ ገደማ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ የአመፅ ቡድኖቹን ተግባር በማዉገዝ ያደረጉት ንግግርም በአሁኑ ወቅት የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል። ተኽለ እዝጊ ገብረ ኢየሱስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ተኽለ እዝጊ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic