መንግሥት 3 የኦነግ አመራሮች እና ሁለት ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይልቀቃቸው
ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2012ማስታወቂያ
ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ በሰጠባቸው እና ውሳኔውን ሳያስፈጽም ከሳምንት በላይ በእስር ያቆያቸውን 3 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች እና ሁለት ጋዜጠኞችን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቃቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። አምንስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ማግለጫው እንዳለው የኦነግ ስራ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ባቲር ፊሌ ፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ገዳ ገቢሳ ፣ የግንባሩ አባል የሆነው ቢሊሱማ አራርሳ እንዲሁም የONN ምክትል ዳይሬክተር ደሱ ዱላ እና ጋዜጠኛ ዋቆ ኖሌ ፍርድ ቤቱ በወሰነላቸው መሠረት ከእስር ሊፈቱ ይገባል ብሏል። መግለጫውን በተመለከተ በአምንስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ኣካባቢ ጉዳዮች አጥኚ አቶ ፍሰሐ ተክሌን ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከኬኒያ በስልክ አነጋግሬአቸኋለሁ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ