የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከፌዴራል ኃይሎች ጋር የቅንጅት እርምጃ ጀመሩ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 3 2014ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉትን የሰላምና ፀጥታ ችግሮች እልባት ለመስጠት የክልሉ እና የፌዴራል መንግስት ኃይላት የተቀናጀ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን አስታወቀ፡፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የጸጥታ መሻሻልን እያመጣ ነው ብሏል፡፡
በሌላ በኩል መንግስት በኦሮሚያ እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ ህዝቡን የሚጎዳ በመሆኑ ለፖለቲካዊ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጠይቋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ