1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእንባ ጠባቂ ዘገባ

ዓርብ፣ ግንቦት 5 2014

የእንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር ዘገባዉ እንዳጋለጠዉ የመታወቂያ፣ የወሳኝ ኩነት ፣ የመሬት እና መሰል አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት ለመስጠት ጉቦ እየጠየቁ ነዉ

https://p.dw.com/p/4BHF3
Äthiopien Addis Abeba | Parlamentssitzung
ምስል Solomon Muchie/DW

                             
የኢትዮጵያ የአገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶች ባለስልጣናትና ባልደረቦች ለሕዝብ መስጠት የሚገባቸዉን አገልግሎቶች በገንዘብ በመሸጣቸዉ የሕዝብ ብሶትና ሮሮ መበርከቱን የፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አጋለጠ። የእንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር ዘገባዉ እንዳጋለጠዉ የመታወቂያ፣ የወሳኝ ኩነት ፣ የመሬት እና መሰል አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች  አገልግሎት ለመስጠት ጉቦ እየጠየቁ ነዉ። ዘገበዉ በቀረበበት ወቅት እንደተነገረዉ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚያደርሱት ጥፋት  አይጠየቁም፤ ለመረጃ ነፃነት ሕግም  ተገዢ አይደሉም።ሕዝቡ ጉቦ ወይም «እጅ መንሻ» እየተጠየቀ፣ በፍትሕ እጦት እያለቀሰ፣ በሚደርስበት በደል እየተማረረም ነዉ-ዘገባ አቅራቢ አድማጮቹ እንዳሉት።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ