1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካእስያ

የእስራኤል ባለስልጣን የትራምፕን ንግግር ተቹ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 19 2013

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግብጽ የሕዳሴውን ግድብ ልታፈነዳው ትችላለች" ማለታቸው፤ በሶስቱ ሃገራት መካከል የሚካሄደውን ውይይት የሚያደናቅፍ በሉዓላዊት ሃገር ኢትዮጵያ ላይ የተቃጣ ጣልቃ ገብነት ነው ሲሉ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ተቃወሙ::

https://p.dw.com/p/3kbx8
Gadi Yevarkan | stellvertretender israelischer Sicherheitsminister
ምስል Privat

የእስራኤል ባለስልጣን የዶናልድ ትራምፕን ንግግር መተቸታቸው

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ «ግብጽ የሕዳሴውን ግድብ ልታፈነዳው ትችላለች» ማለታቸው፤ በሦስቱ ሃገራት መካከል የሚካሄደውን ውይይት የሚያደናቅፍ በሉዓላዊት ሃገር ኢትዮጵያ ላይ የተቃጣ ጣልቃ ገብነት ነው ሲሉ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ተቃወሙ። ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዊው የእስራኤል የሀገር ደህንነት ምክትል ሚኒስትር ደስታው ጋዲ ይቫርካን በተለይ ለዶይቼ ቨለ /DW/  ትራምፕ በሱዳን-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ የትብብር ስምምነት ላይ ይህን አወዛጋቢ ሃሳብ መሰንዘራቸው  ዓለም አቀፍ ሕግጋትን የሚጥስና የዲፕሎማሲ መርሆችን የሚፃረር ነው ብለዋል። 


እንዳልካቸው ፍቃደ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ