1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የእሥራኤልና ሔዝቦላ ጦርነት የፈጠረው ስጋት

ገበያው ንጉሤ
ረቡዕ፣ መስከረም 15 2017

እስራኤል ከዐሥር ወራት በፊት በራሷና ምራባውያንን በአሸባሪነት የተፈረጀው ሐማስ በዜጎቿ ላይ የፈጸመውን ጥቃትና እገታ ተከትሎ፤ በጋዛና ምራባዊ የፍልስጠኤም ግዛት የከፈተችው ጥቃት አልተቋጨም ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ፤ በእራኤልና ሊባኖስ ደንበር ሌላ ጦርነት ቀጥሏል ።

https://p.dw.com/p/4l4Mb
Libanon Angriffe Israel Krieg
ምስል Baz Ratner/AP/picture alliance

የእሥራኤልና ሔዝቦላህ ጦርነት የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት

እስራኤል  ከዐሥር ወራት በፊት በራሷና ምራባውያንን በአሸባሪነት የተፈረጀው ሐማስ በዜጎቿ ላይ የፈጸመውን ጥቃትና እገታ ተከትሎ፤ በጋዛና ምራባዊ የፍልስጠኤም ግዛት የከፈተችው ጥቃት አልተቋጨም።  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ፤ በእራኤልና ሊባኖስ ደንበር ሌላ ጦርነት ቀጥሏል ።

ባለፈው ሳምንት በሔዝቦላህ አባላት እጅ እንዲገቡ የተደረጉ የኤሌክትሮኒክስ መልእክት መቀበያ መሣሪያዎችና  የመገናኛ ሬዲዮኖች ፍንዳታ፤ በርካታ ሰዎች መሞታቸውና ከሦስት ሺ በላይ ደግሞ እንዲቆስሉ  የሚታወስ ነው ። ባልፉት ሁለት ቀናት በደንበሩ አክባቢና የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ጭምር በተጀመሩ ጦርነቶችና የአየር ድብደባዎችሞ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የሞቱና  በሺዎች የሚሆኑ የቆጠሩ መሆኑ ተገልጿል።

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ  ጆሴፍ ቦርየልም ከሂዝቦላ ጋር የተተቀሰቀሰውን ጦርነት በማውገዝ  ከኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ይህንኑ በሁለት ቀናት በሊባኖስ የደርሰውን ሰብአዊ  ጉዳት አረጋግጠዋል፤ “ ካማክሰኞ ወዲህ ብቻ  500 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከአራት ሸ አራት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል” በማለት ከጦርነቱ ሰለባዎችና ጉዳተኖች ውስጥም በርክታ ህጻናት የሚገኙባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ጆሴፍ  ቦርየል አክለውም፦ ይህ ግጭት ሁለቱ ወገኖች ወደለይለት ጦርነት እየገቡ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን  በመግለጽ፤ ሊያስክትል የሚችለውን ጉዳትና መዘዙንም አስገንዝበዋል። በዚህ ምክኒያት በአካባቢውና በዓለም ሰላም ጭምር ሊፈጠር የሚችለውን ቀውስ በመጥቀስም፤ ይህን ለመክላከል ግን በመካከከለኛው ምስራቅ ሰላም ማስፈኑ ወሳኝ መሆኑን  አስገንዝበዋል፤ የመጀምሪያው የሰላም እርምጃ በጋዛ ተኩስ ማቆም መሆኑን አጽናኦት በመስጠት!

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጥሪ

የመግንስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬም በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ንግግር፤  የመካከለኛው ምስራቅ ችግር የዓለማችን አንዱና ትልቁ ችግር መሆኑን በማንሳት፤ግጭቶች እንዳይሰፉና እንዳይባባሱ ሁሉም የሚችለውን ማድረግ የሚገባው መሆኑን አስገንዝበዋል።” አለም ሊባኖስን ሌላ ጋዛ ስትሆን ማየት አይሻም” በማለትም ሁሉም  ውጥረቱ እንዲረግብና ጦርነት እንዲቆም ድምጹን ማሰማት የሜገባው መሆኑን በግምባር በጉባኤው ላይ ድምጻቸውን አሰምተዋል ።

ደቡባዊ ሊባኖስ ። ፎቶ፦ ከማኅደር
ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ የሚገኝ አውራ ጎዳና ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Ibrahim Amro/AFP/Getty Images

ሰሚ የሌለው የዓለምአማቀፉ ማኅብረሰብ ጩኸት

ከአረብ አገሮች በተጨማሪ አሜሪካና ምርባውያን አገሮች ጭምር የእስራኤልና ሂዝቦላ ግጭት እንዳያድግ እያሳሰቡ ነው። ቻይናና ሩሲያም የሁለቱ ወገኖች ግጭት አካባቢውን ወደ ጦርነትና ትርምስ እንዳያስገባው አስጠንቅቀዋል። እስራኤል ግን በተለይም የጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒይሁ መንግስት ማንንም እንደማይሰማ ነው የሚነገረው።፡እንደውም አሉ በቤይሩት የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ፖሮፊሰር የሆኑት ራሚ ክሆሪል፤ “ እስራኤል አሁን እያደረገች ያለው ጋዛ ላይ ያደረገችውን ነው። ህዝቡን እንደመንጋ መንዳትና በቦምብ መደብደብ” በማለት ሌላ አይነት ግን አዲስ ዘዴ መጠቀም ካልተቻለ በስተቀር እስራኤል  የማንንም ጥሪና ውግዘትም የማትሰማ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

በእስራኤል ፖሊሲ ላይ ለውጥ ሊያስክትል የሚችል ርምጃ

በመካከለኛው ምስራቅ የምርምር ተቋም  ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት  ሚስተር ከሃሊድ ኤልጂንዲይ እንደሚሉትም እስራኤል በተጨባጭ ጫና ሌፈጥሩ ከሚችሉ እርምጃዎች ውጭ፤ ለየትኛውም ውግዘትና ጩኸት ደንታ የላትም ። “ በእስራኤል ላይ ተጨባጭ እርምጃ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ውግዘትና ወቀሳ ለውጥ አያመጣም። በጋዛ ላይ እይወሰደች ባለው እርምጃ ብዙ ክስና ወቀሳ ድርሶባታል ግን አላቆመችም። ስለዚህ በወቀሳና ውግዘት ብቻ እስራኤል ላይ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። ኢስራኤልን የሚያሳስባት ብቸኛው እርምጃ የጦር መሳሪያ እቀባ  ብቻ ነው በማለት ከዚያ በመለስ  ያለው ሁሉ ግን ባዶ ጩኸ ትነው የሚሆነው ብለዋል ።

እስራኤል በጋዛም ሆነ በሊባኖስ እይወስደች ባለው ርምጃ ምክንያት  ከሚሰሙት ውግዘቶችና ወቀሳዎች ውጭ የመሣሪያ ማቀብም ይሁን ሌላ ተጨባጭ ርምጃ የሚወሰድ ስለመሆኑ አለምሰማቱ ደግሞ ሊባኖስ በተለይም ቤይሩት ሀተኛዋ  ጋዛ ላለመሆኗ ዋስትና የለም ነው የሚሉት ታዛቢዎች ።

ገበያው ንጉሤ

ታምራት ዺንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ