የኢትዮ-ሱዳን ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ
ማክሰኞ፣ ጥር 4 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።የሱዳን ጦር የኢትዮጵጵያን ድንበር ዘልቆ ተጨማሪ ግዛቶች መቆጣጠሩን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ አስታዉቋል።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ግዛቶችን መዉረሩን እንዲያቆም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም እስካሁን ሰሚ አላገኘችም።አምባሳደር ዲና አክለዉ እንዳሉት ሱዳንና ግብፅ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን ለማጓተት፣ ሱዳን የተጠለሉ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሐገራቸዉ እንዳይመለሱ ለማድረግም እያሴሩ ነዉ።
ሠለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ