1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ዕርቅ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 19 2013

የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተባለ ስብስብ አሉኝ ብሏቸው በነበሩ የአስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጋር ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት መፍትሔ ማግኘቱ ተገለፀ። የተነሱ ጥያቄዎችን በአንድነት መፍታት እንደታመነበት እና እርቅ ለማውረድ ላለፉት ስድስት ወራት የተንቀሳቀሰው ኮሚቴ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3kc7F
Äthiopien Addis Ababa | Orthodoxe Kirche | Belay Mekonnen
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እርቅ

የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተባለ ስብስብ አሉኝ ብሏቸው በነበሩ የአስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጋር ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት መፍትሔ ማግኘቱ ተገለፀ።በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስር በሚቋቋም ጠንካራ አካል በኩል የተነሱ ጥያቄዎችን በአንድነት መፍታት እንደታመነበት እና እርቅ ለማውረድ ላለፉት ስድስት ወራት የተንቀሳቀሰው ኮሚቴ አስታውቋል።የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንንና ኮሚቴያቸው ከድርጊታቸው ተቆጥበው በንሥሓ እስኪመለሱ ድረስ ከየካቲት 11 ቀን 2911 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስትያን የተሰጣቸው ክህነት መያዙን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቆ ነበር። ቅዱስ ሲኖዶሱ በቀጣይ የስምምነቱን ዝርዝር ጉዳይ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል። 


ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ