የኢትዮጵያ ቀዉስ ወደ አፍሪቃ ቀንድ እንዳይሰፋ ስጋት መቀስቀሱ   | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ቀዉስ ወደ አፍሪቃ ቀንድ እንዳይሰፋ ስጋት መቀስቀሱ  

አስር ወራት በፊት በትግራይ የተቀሰቀሰዉ ጦርነት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በመዛመቱ፤ ቀዉሱ ወደ አፍሪካ ቀንድ ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋትን ደቅኗል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ገለፀ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:14

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን


አስር ወራት በፊት በትግራይ የተቀሰቀሰዉ ጦርነት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በመዛመቱ፤ ቀዉሱ ወደ አፍሪካ ቀንድ ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋትን ደቅኗል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ገለፀ። የድርጅቱ ኮሚሽነር ሚሸል ባችሌት ትንናት ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ላይ በጀመረዉ 48ኛ የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ዓመታዊ ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት፤ በትግራይ ክልል የተነሳው ጦርነት ወደ አጎራባቾቹ አፋርና አማራ ክልሎች መዛመቱ ብሎም በአገሪቱ ከሚታየዉ የእርስ በርስ ግጭቶች ጋር ተዳምሮ ወደ አፍሪቃ ቀንድ እንዳይስፋፋ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ኮሚሽነርዋ በትግራይ ክልል ስለተፈፀመዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ለማጣራት ያሳየዉን እርምጃም  አድንቀዋል።   

ገበያዉ ንጉሴ 
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ 
 

Audios and videos on the topic