የኢትዮጵያ ለአፍሪቃዊ ችግር አፍሪቃዊ መፍትሔ አቋም
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 7 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር የምታደርገው ድርድር ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ በሳምንታዊ መግለጫው እንዳለው ግብጽ እና ሱዳን ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ ጥቅሞቻቸውን ሊያስጠብቁላቸው የሚችሉ ሌሎች አካላት የህብረቱን ሚና እንዲጋሩ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ አትቀበልም ብሏል። የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን ጨምሮ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይም የውች ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ዝርዝር መግለጫ ሰጥተዋል። መግለቻውን የተከታተለው ሰለሞን ሙጬ ተከታዩን ዘገባ ከአዲስ አበባ ልኮልናል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ