1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

48 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በጅቡቲ የባህር ዳርቻ መሞታቸውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረጋገጠ

ዓርብ፣ መስከረም 24 2017

በአደጋው 48 ፍልሰተኞች ሲሞቱ፣ 197 ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የተባለው አካባቢ የሚገኝ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸውንም አስታውቋል። የተቀሩትን 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ሥራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉንም ኤምባሲው ገልጿል። ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ መቻሉንም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4lQCM
ምሥራቅ ጅቡቲ የሚገኘው የዳመርጆግ ወደብ
ምሥራቅ ጅቡቲ የሚገኘው የዳመርጆግ ወደብምስል Solomon Muche/DW

48 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በጅቡቲ የባህር ዳርቻ መሞታቸውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረጋገጠ

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከየመን ወደ ጅቡቲ 320 "መደበኛ ያልሆኑ" ያላቸውን ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር ዳርቻ አከባቢ ሲደርሱ በደረሰው አደጋ የዜጎች ሕይወት አልፏል ሲል በይፋዊ የፌስቡክ ማሕበራዊ መገናኛ ዐውታሩ ገልጿል።

አደጋውን ተከትሎ 48 ፍልሰተኞች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 197 ፍልሰተኞች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የተባለው አካባቢ ያየሚገኝ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸውንም አስታውቋል። የተቀሩት 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ሥራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉንም ኤምባሲው ገልጿል።

መቋጫ ያላገኘው የሳውዲ ስደተኞች እሮሮ

"እስከአሁን በስፍራው በተደረገው የዜጎች ማጣራት ሂደት ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ ተችሏል" ያለው ኤምባሲው በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት በየጊዜው እያደረሰ ያለውን ሞት ለመቀነስ ሁሉም ተቋማት በርብርብ ሊሰራ እንደሚገባ ጠይቋል። 

 

Jemen | Migrantenboot vor der Küste von Ras al-Ara
ምስል Nariman El-Mofty/AP Images/picture alliance

አደጋው ከደረሰ በኋላ መንግሥት ምን እየሠራ እንደሆን ለመጠየቅ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብንደውልም ለጊዜው ምላሽ አላገኘንም። ባለፈው ሳምንት መግለጫ የሰጡት የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚየንማር ዜጎች እየተጭበረበሩ በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ ሞት ቀጣና እያመሩ እንደሆነ ተገንዝበነል" ብለው ነበር።የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መቃብር በማላዊ

ለመሆኑ የዜጎች የሕገ ወጥ ዝውውር እና ፍልሰት ማብቂያ ያጣው ለምን ይሆን በሚል በጉዳይ ላይ ምርመር ለሚያደርጉት ዶክተር ግርማቸው አዱኛ በቅርቡ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር።

የተሻለ ኑሮ ፈላጊ ሰዎች በተደጋጋሚ በሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች መረብ ውስጥ እየገቡ ያሰቡ ያለሙበት ሳይደርሱ የበረሃ እና የባሕር ሲሳይ እየሆኑ ሲቀሩ መስማት በእጅጉ ተለምዷል።ሌላው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመከራ መንገድ ፤ ታይላንድ ባንኮክ

የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻም፣ መተላለፊያም የሆነቸው ኢትዮጵያ ብዙ ዜጎቿ የዚህን መሰሉ ችግር ሰላባ መሆናቸውም በየጊዜው የሚሰማ ጉዳይ ነው። 

 

ሰሎሞን ሙጬ

 ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ