የኢትዮጵያውን ብሶት ከምሥራቅ ሱዳን | ኢትዮጵያ | DW | 12.08.2014
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውን ብሶት ከምሥራቅ ሱዳን

በምሥራቃዊው ሱዳን ገዳርፍ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሰበብ-አስባቡ የአንዳንድ አክራሪ ቡድኖች የጥላቻ ሰለባዎች ሆንን» ሲሉ ብሶታቸውን ገለጡ። በ« ኤስ ኤም ኤስ » የሚደርሱን አጫጭር መልእክቶች እንደሚሉት ከሆነ ብዙዎች

Karte Sudan Englisch

ሰዎች ያላበሳቸው የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፤ ደብዛቸው የጠፋም ጥቂቶች አይደሉም። በጅምላ ታፍሰው የታሠሩም አሉ። ምክንያቱ ፣ መንስዔው ምን ይሆን? በዚያው በገዳርፍ አካባቢ የሚኖሩና የድርጊቶችን ሂደት የተከታተሉ አንድ ኢትዮጵያዊ አብራርተውልናል።

ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገሮች በደል ደረሰብን፤ የግፍ ርምጃ ተፈጸመብን በማለት፤ ዋይታ ፣ ብሶት ሲያሰሙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ሱዳን ውስጥ በመዲናይቱ በካርቱም ፤ ከሳምንት በፊት ስለተፈጸመ ማዋከብ ድብደባ፤ ማሠርና የመሳሰለ አስከፊ ሁኔታ መዘገባችን ይታወስ ይሆናል የዛሬው ብሶት የደረሰን ከዚያ እጅግ ራቅ ባለው ምሥራቃዊው የአገሪቱ ከፊል ነው። ስለተፈጠረው ችግር ጉዳዩን በጥሞና የተከታተሉ አንድ ኢትዮጵያዊ እንደሚከተለው አብራርተውልናል።

በተጠቀሰው አካባቢ ኢትዮጵያውያኑን ሲያስጨንቅ የሰነበተው ጉዳይ ፤ እንደሚባለው ፤ አንድ አክራሪ ቡድን የፈጠረው ደም አፋሳሽ ውዝግብ አሁን እስከምን ድረስ ረገብ ያለ መሆኑንም ጠይቀናቸው ነበር።

አሁን በኢትዮጵያዊው ማሕበረሰብ ያለው ሁኔታ እስከምን ድረስ የተረጋጋ እንደሆነ ጠባቂም ሆነ ጉዳያቸውን የሚከታተል ጠበቃ ስለመኖር አለመኖሩም ጠይቀናቸው ነበር።

በካርቱም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዋና ኀላፊ ኧል ናይም፤ ጉዳዩን ኮሚሽኑ በጥሞና ከመረመረ በኋላ መግለጫ እንደሚያወጣ አስረድተዋል።

ተክሌ የኋላ

 • ቀን 12.08.2014
 • አዘጋጅ
 • አስተያየትዎ: ?????!
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1CtAL