የኢሰመኮ የመብት መከበርን ጉዳይ በኪነ ጥበብ የማስፋፋት ጥረት
ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2016የመብት መከበርን ጉዳይ በኪነ ጥበብ የማስፋፋት ጥረት
በቂ የመኖሪያ ቤት የማግኘት እና በሕይወት የመኖር መብት ላይ ያተኮረው ሦስተኞው የኢትዮጵያ ሰብዓ መብቶች ኮሚሽን የፊልም ፌስቲቫል "ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቶቹ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ ሆነው እንዲቀርቡ ጥሪ ቀረበ።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ለዚህ ዓመት ለዕይታ የሚቀርቡ አጫጭር ፊልሞች እና ፎቶግራፎች "በሕይወት የመኖር መብት ወይም በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ" እና ልዩ ትኩረት የሚሹ ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን፣ ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን ጭምር ባካተተ መልኩ እንዲቀርቡም ተጠይቋል። ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል በሚገኝ ጊዜያዊ የሰዎች ማቆያ ቦታ ሕይወት ማለፉን ሲገልጽ፤ ክልሉ በበኩሉ የሰዎች ማቆያ የለም ይላል
በጦርነት እና ግጭት ፣ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ፣ ውጥረት በበዛበት የጎሳ አመለካከት እና ሌሎች ምክንያቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተስተዋለባት ባለችው ኢትዮጵያ መሰል የመብት ጥሰቶች ፊልምን በመሳሰሉ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንዲንፀባረቁ ማድረጉ ከተደራሽነት አንፃር ጠቃሚ መሆኑም ታምኖበታል።
ሦስተኛው የኢሰመኮ የፊልም ፌስቲቫል
የሰብአዊ መብቶችን መከበር ለማበረታታት ኢሰመኮ ከሚጠቀማቸው አማራጮች የመብት መከበርንም ሆነ ጥሰቶችን በኪነ ጥበብ ዘርፍ ማካተትና እንዲዳሰሱ ማበረታታት ሲሆን የዚህኛው ዓመት የኮሚሽኑ የፊልም ፌስቲቫል ትኩረቶች ሆነው እንዲንፀባረቁ የተፈለጉት አንኳር የመብት ጉዳዮች ኢትዮጵያ ውስጥ በአሳሳቢነታቸው የቀጠሉት በሕይወት የመኖር እና በቂ የሆነ የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብቶች ናቸው።
ኮሚሽኑ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ይህንን ሥራ ሲያከናውን የመጣ ሲሆን በዚህኛው ዓመት ሥራዎች አስተማሪ ሆነው ለዕይታ እንዲቀርቡ የተመረጡባቸው የኪነ ጥበብ ዘርፎች አጫጭር ፊልሞች እና ፎቶግራፎች ናቸው።
ኢሰመኮ እንደሚለው የሰብዓዊ መብቶች በስፋት በኪነ ጥበብ ሥራዎች ውስጥ ትኩረት አግኝተው እንዲዳሰሱ ማድረጉ "ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን" ማየት የሚለውን ራዕዩን ለማሳካት አቅም የሚሰጠው ነው።ከእናቶቻቸው ጋር የሚታሰሩ ሕጻናት አያያዝ “አሳሳቢ” እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በኢሰመኮ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ እስራኤል ሰለሞንን ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀናቸው ሥራው ውጤት እየተያበት መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህ ውድድር ተሳትፎ ማድረግ የሚሹ ሁሉ እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ሥራዎቻቸውን ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ እድል ቀርቦላቸዋል። በሥራዎቻቸውም በቂ ስለሆነ የመኖሪያ ቤት የማግኘት እና በሕይወት የመኖር መብቶች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቱ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ የኪነጥበብ ሥራዎች እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን ጨምሮ ሴቶችን እና አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ስደተኞችን ያካተቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል።
የሰብዓዊ መብቶችን በመደበኛ ትምህርት የማካተት ጥረት
ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በመደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ በትምህርት ሥርዓቱ እንዲካተት ለማድረግ ግፊት እያደረገ መሆኑን ካስታወቀ ቆይቷል።
ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ሲሰጥ የነበረው የሥነ ዜጋ እና የሥነ ምግባር ትምህርት "የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን የሚጣረሱ አንዳንድ አስተሳሰቦችን አግኝቸበታለሁ" በማለት "ሰብአዊ ክብር፣ ነጻነት እና ፍትሕ ለሁሉም" በሚል ሁለተኛውን ዙር ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች የፊልም ፌስቲቫል ባለፈው ዓመት በአምስት ከተሞች አከናውኖ ነበር።
የኢሰመኮ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ክፍል ዳይሬክተር አቶ እስራኤል ሰለሞን ሥራው ከዓመት ዓመት ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል።ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀብሩ ፈንጂዎች እንዲመክኑ ኢሰመኮ ጥሪ አቀረበ
በጦርነት እና ግጭት ፣ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እና የመፈራረጅ ልማድ ፣ ውጥረት በበዛበት የጎሳ አመለካከት እና እነሱ እና እኛ በሚሉ ምክንያቶች እና ያንን ተከትሎ በሚፈጠሩ ልዩነቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተስተዋለ መሆኑን በዘርፉ ላይ የሚሠሩ ተቋማትና ግለሰቦች አዝማሚያው የባሰ እንዳይወሳሰብ ለመፍትሔው እንዲሠራ ከመጎትጎት ቦዝነው አያውቁም።
መሰል የመብት ጥሰቶች ፊልምን በመሳሰሉ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንዲንፀባረቁ በማድረጉ ከተደራሽነት አንፃር ሕዝብገልፀዋል።ንዛቤ እንዲያገኝ የማድረጉን አስፈላጊነት በመያዝ ኢሰመኮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ