1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በርካታ ተሳታፊዎች በታደሙበት ዛሬ በአዲስ አበባ ተከበረ፡፡

ቅዳሜ፣ መስከረም 21 2015

በጥብቅ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ የተካሄደው የዘንድሮ ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በጉልህ የተሰሙ የተቃውሞ ድምጾችም ተሰምቶበታል፡፡

https://p.dw.com/p/4Hcth
Äthiopien Addis Abeba | Oromos feiern Irreecha-Fest
ምስል Seyoum Getu/DW

ኢሬቻ ፊንፊኔ

ስነስርዓቱ ከማለዳ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ አባገዳዎች ወንዙን ባርከው በምርቃት በጀመሩት ስርዓት ነው የተካሄደው፡፡
በኢሬቻ ክብረ በዓሉ ላይ የወለጋ ግድያ እና መፈናቀል ይቁም የሚሉ የተቃውሞ ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡
በጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር የተከበረው ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ የተሳታፊዎቹ ቁጥር ከ2012 ዓ.ም. ክብረ በዓሉ ጋር ባይወዳደርም በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳሚን ግን ተሳትፈው ስርዓቱን አድምቀውታል፡፡
 ዛሬ ማለዳውን ከ12 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ስነስርዓት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያው ባሉ የኢሬፈና ቦታዎች የተከበረው ኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ በአባ ገዳ ምርቃት እና በእናቶች ህብረ ዜማ ነው ነው የተጀመረው፡፡
ዘንድሮ በአዲስ አበባ ለተከታታይ አራተኛ ዓመት በተከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ የታደሙ ተሳታፊዎች ለዶይቼ ቬለ እንዳሉትም የአንድነትና የሰላም መድረክ ነው ያሉት ኢሬቻ በተለይም በኦሮሞ ህዝብ መካከል ለሚስተዋለው ልዩነት አንድነትን እንዲያመጣ ጠይቀዋል፡፡ ታዳሚያኑ በመላው ኢትዮጵያ ለሚካሄደውም ጦርነት የሰላም ጥሪ አሰምተዋል፡፡በጥብቅ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ የተካሄደው የዘንድሮ ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በጉልህ የተሰሙ የተቃውሞ ድምጾችም ተሰምቶበታል፡፡ የተቃውሞ ድምጾቹ በወለጋ የዜጎች ግድያ እንዲቆም፣ የኦሮሚያ ወሰን እንዲከበርና የፖለቲካ እስረኞች ያሏቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፖለቲከኞች እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ከተነሱ ጉልህ ተቃውሞዎች ናቸው፡፡ ስማቸውን መግለጽ የማይፈልጉ የተቃውሞ ድምጹን ካሰሙት አንዷ፤ “በኦሮሚያ በተለይም በወለጋ እየሆነ ያለው መቆም አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ እናቶች በወለጋ ለዘመናት ሲያነቡ ቆይተዋል፡፡ ይህ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው፡፡ ደም መፋሰሱ መቆም አለበት፡፡ ምን አጠፋ የወለጋ ህዝብ፡፡ አሁን እየሰማህ ያለው ተቃውሞም መሰረታዊ እና ትክክለኛ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡” በማለት የተቃውሟቸውን ምክኒያት ለዶይቼ ቬለ አብራርተዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
 

Äthiopien Addis Abeba | Oromos feiern Irreecha-Fest
ምስል Seyoum Getu/DW