1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚአፍሪቃ

የአፍሪቃን የኤልክትሮኒክ ግብይት አቅምን መክፈት

ቅዳሜ፣ ሰኔ 1 2016

በኤሌክትሮኒክ የሚፈፀም ግብይት በአፍሪቃ እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2025ዓ.ም ድረስ እስከ 75 ቢሊዮን ዶላርዕድገት ያስገኛል ተብሎ ተገምቷል። በአፍሪቃ በኤሌክትሮኒክ ገበያ ላይ፤ እንደ አማዞን ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ መድረክ እየወጡ ነው። በአፍሪቃ የኦንላይን ግብይት ቀጣይ የእድገት ርምጃ ወዴት ይሆን?

https://p.dw.com/p/4gnxD
በአፍሪቃ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ከሌላዉ ዓለም ሲነፃፀር አሁንም መጀመሪያ ደረጃ ላይ ነው
በአፍሪቃ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ከሌላዉ ዓለም ሲነፃፀር አሁንም መጀመሪያ ደረጃ ላይ ነው ምስል Guox Jun/Xinhua/IMAGO

የአፍሪቃን የኤልክትሮኒክ ግብይት አቅም መክፈት

የአፍሪቃን የኤልክትሮኒክ ግብይት አቅምን መክፈት     


በኤሌክትሮኒክ የሚፈፀም ግብይት በአፍሪቃ እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2025ዓ.ም ድረስ እስከ 75 ቢሊዮን ዶላርዕድገት ያስገኛል ተብሎ ተገምቷል። በአፍሪቃ በኤሌክትሮኒክ ገበያ ላይ፤ እንደ አማዞን ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ መድረክ እየወጡ ነው። በአፍሪቃ የኦንላይን ግብይት ቀጣይ የእድገት ርምጃ ወዴት ይሆን?  
አፍሪቃውያን የኦንላይን ግብይት ማለትም የኤሌክትሮኒክ ግብይት ቀስ በቀስ መድረኩን እየያዘ ነዉ። ይሁን እንጂ በአፍሪቃ ያለዉ ይህ የግብይት ዘርፍ  እንደ እስያ፣ አውሮጳ እና አሜሪካ ዉስጥ ከሚገኙ ግዙፍ እና ጥቃቅን የኤልክትሮኒክ ማለትም ኦን ላይን ገበያዎች ጋር ሲነጻጸር አሁንም በአፍሪቃ ያለዉ ገና መጀመርያ ደረጃ ላይ ነዉ። ሜኪንሴይ የተባለዉ ዓለም አቀፍ ተቋም ባስቀመጠዉ ትንበያ መሰረት፤ በጎርጎረሳዉያኑ 2025 ዓ.ም በአፍሪቃ በኤልክትሮኒክ በሚፈፀም ግብይት 10% የሚሆነው የችርቻሮ ንግድ ትላልቅ ንግዶች በሚካሄዱባቸዉ በናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪቃ እና በግብፅ ሊሸፍን እንደሚችል ይጠቁማል።  እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ የኤልክትሮኒክ የግብይት ዘርፍ በአፍሪቃ ከፍተኛ አቅም ያለው ቢሆንም፣ ከባህላዊ እና ከአቅርቦት ጋር ተግዳሮቶች ገጥመውታል።   
በአፍሪቃ ትልቁ የኤልክትሮኒክ ገበያ ጁሚያ ይባላል። ጁሚያ በወር 23 ሚሊዮን ግብኝቶችን የሚያስተናግድ የኤልክትሮኒክ ግብይት  ኩባንያ ነው። ከጁምያ ቀጥሎ Takealot.com 10 ሚሊዮን ወርሃዊ ግብይትን የሚያስተናግድ እና 96% ያህሉ ግብይት ደቡብ አፍሪቃ ባለ የኦንላይን መድረክ የሚፈፀም ነዉ።     
በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚገኘዉ Souq.com፣ ብሎም፤ በ2017 ዓም በመካከለኛው ምስራቅ ንግድ የጀመረዉ አማዞን ፣ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ወርሃዊ ጉብኝቶችን ይፈፅማሉ። አብዛኛዎቹ ግብይቶች የሚፈፀሙት ከግብፅ ነው። በሌላ በኩል ሻይን SHEIN የተባለዉ የፋሽን ነገሮችን የሚቸረችረዉ የንግድ መተግበርያ በደቡብ አፍሪቃ ታዋቂነትን አግኝቷል።   


የኤልክትሮኒክ ግብይት እድገት ፈተናዎች
በአፍሪቃ የኤልክትሮኒክ ንግድ እንዲስፋፋ፣ መስተካከል ያለባቸው ተግዳሮቶች አሉ። DW ያነጋገራቸው አንዳንድ ናይጄሪያውያን ተአማኒነት እና ቀልጣፋ የአቅርቦት አገልግሎት ደንበኛን ለማርካት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። «እነዚህን ምርቶች የሚያስተዋውቁ ሰዎች ተአማኒነት እና ከዋጋ አንጻር እንዴት እንደሚሸጡ እና እቃዉን እንዴት እንደሚያደርሱ ማወቅ አለባቸዉ። አንዳንዴ አንድ ነገር ያስተዋውቃሉ፤ ከዝያ እቃዉን አይተዉ ያዛሉ። ግን የታዘዘዉ እቃ ሲደርስ፤ እቃዉ ዋጋዉ ነዉ ብለህ የምትከፍለዉ አይደለም። »
ሌሎች በናይጀርያ የሚገኙ የኤልክትሮኒክ ገብያተኞች እንደሚሉት የደንበኞች ማዕከላት ለሚደርሱ ችግሮች ማብራርያ ለመስጠት ዝግጁ አይደሉም አልያም አይገኙም።  ባለፈው ወር ግዙፉ የኤልክትሮኒክ መገበያያ አማዞን በደቡብ አፍሪቃ ሥራዉ ጀምሯል። ይህ ግዙፍ የኦን ላይን መገበያያ መድረክ እንደ Takealot ያሉ በደቡብ አፍሪቃ እዉቅ የኤልክትሮኒክ ግብይት ኩባንያዎችን እየሸፈነ እና ብዙ ቸርቻሪዎችን የንግድ ስልታቸዉን እንዲቀይሩ እያስገደ ነው። 

የናይጀርያዉ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ጁሚያ ከናይጀሪያ፣ ከግብጽ፣ ከሞሮኮ፣ ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪቃ እና ከሌሎች ሀገራት የሚመጤ ሽያጮን ያቀርባል።
የናይጀርያዉ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ጁሚያ ከናይጀሪያ፣ ከግብጽ፣ ከሞሮኮ፣ ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪቃ እና ከሌሎች ሀገራት የሚመጤ ሽያጮን ያቀርባል። ምስል Issouf Sanogo/AFP/Getty Images

በኤሌክትሮኒክ ግብይት ችርቻሮ የተሰማራችዉ ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ፓዉላ ማሴኮ የአማዞን ወደ ደቡብ አፍሪቃ መምጣት እንደስዋ ያሉ፤ አነስተኛ ቸርቻሪዎችን ሊጎዳ ይችላል፤ «አማዞን ወደ ደቡብ አፍሪቃ የችርቻሮ ንግድ መምጣት እንደ እኔ ላሉ ትናንሽ ነጋዴዎች ጥሩ ነገር አይደለም።  ምክንያቱም ከእኛ የበለጠ ሀብት ስላላቸው እና ምናልባትም ከእኛ ባነሰ ዋጋ ይኖራቸዉ ይሆናል። ታድያ እኛ በሕይወት መትረፍ እንችላለን? ስለዚህ በንግድ ሥራ ላይ መለወጥ እና ከሁኔታዎች ጋር መላመድ አለብን ለማለት ነው። ስለዚህ በዚህ አይነቱ የንግድ ዘመን መለወጥ እና ከሁኔታዎች ጋር ለመላመድ መሞከር አለብን።»

ኦኬሪ ኑቲጂናዞ / አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ