1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፋር ጥቃት                                                 

ሐሙስ፣ ጥር 26 2014

በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአፋር ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ አዲስ ጥቃት  መክፈቱን  የአፋር ክልል ባለስልጣናትና ነዋሪዎች አስታወቁ።ሕወሓት ባለፈዉ ታሕሳስ ከአብዛኞቹ የአማራና የአፋር ክልልሎች ከወጣ በኋላ ጋብ ብሎ የነበረዉ ዉጊያ ካለፈዉ ሳምንት ወዲሕ በአፋር ክልል እንዳዲስ ማገርሸቱ በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር።

https://p.dw.com/p/46UGG
Äthiopien l Geflüchtete Menschen in Afar Iwa
ምስል Seyoum Getu/DW

ካለፈዉ ሳምንት ወዲሕ በአፋር ክልል ጥቃቱ አገርሽቶአል

 በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአፋር ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ አዲስ ጥቃት  መክፈቱን  የአፋር ክልል ባለስልጣናትና ነዋሪዎች አስታወቁ።ሕወሓት ባለፈዉ ታሕሳስ ከአብዛኞቹ የአማራና የአፋር ክልልሎች ከወጣ በኋላ ጋብ ብሎ የነበረዉ ዉጊያ ካለፈዉ ሳምንት ወዲሕ በአፋር ክልል እንዳዲስ ማገርሸቱ በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር።አዉሮጳ የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች በአፋር ሕዛብ ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት መከላከያ ጦር አልተከላከለም በማለት ትናንት ባደባባይ ሰልፍ ወቅሰዉ ነበር።የአፋር ክልል ባለስልጣናት ዛሬ እንዳሉት ሕወሓት ሶስት ወረዳዎችን ተቆጣጥሯል።ሕወሓት ትናንት ለዛሬ አጥቢያ በከፈተዉ ጥቃት በተለይ በረሐሌና ኮነባ የተባሉ አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ጭምር እያጠቃ ነዉ።ዶቸ ቬለ ከሕወሓት በኩል ማረጋገጪያም ማስተባበያም ማግኘት አልቻለም።የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ ግን የአፋር ባለስልጣናትና ነዋሪዎችን አነጋግሯል። 

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ