የአድዋ ድል በዓል አከባበር ዉዝግብና የህዝብ አስተያየት
ዓርብ፣ የካቲት 22 2016ማስታወቂያ
ከኢትዮጵያውያን አልፎ የጥቁር ህዝብ ድል ተደርጎ የሚነሳው የአድዋ ድል በዓልበአንድነት እና በህብረት እንዲከበር አስተያየት ሰጪዎች ጠየቁ፡፡ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ እየጎላ የመጣው ውዝግብ መወገድ አለበት።128ኛው የአድዋ ድል በዓል፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች ነገ ይከበራል።አምና 127ኛው የድል በዓልሲታሰብ በተለይም ፒያሳ በሚገኘው የሚኒሊክ አደባባይ አከባቢ በተፈጠረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በርካቶች በአስለቃሽ ጭስ መበተናቸው አይዘነጋም፡፡
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ