1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኦፌኮ አባል ከእስር ተለቀቁ

ቅዳሜ፣ ጥር 1 2013

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነባህሪ ኮሌጅ ዲን እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባል ዶ/ር ሁሴን ከድር ከመንፈቀ ዓመት በኋላ ከእስር ተለቀቁ፡፡ ዶክተር ከድር ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ በዋስትና እንዲለቀቁ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ሳይከበሩ እንደቆዩ ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል

https://p.dw.com/p/3nj8t
Äthiopien Oromo Federalist Congress
ምስል Seyoum Getu/DW

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኦፌኮ አባል ከእስር ተለቀቁ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነባህሪ ኮሌጅ ዲን እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባል ዶ/ር ሁሴን ከድር ከመንፈቀ ዓመት በኋላ ከእስር ተለቀቁ፡፡

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በሰበታ ተይዘው ወደ አጋርፋ የተወሰዱት ዶ/ር ሁሴን ከድር በወቅቱ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው እንዲለቀቁ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር፡፡

ይሁንና ተጠርጣሪውን ሊለቃቸው ያልወደደው ፖሊስ ወደ አዲስ አበባ በማምጣት ዳግም በለገጣፎ ለፍርድ ቤት አቅርቦአቸው እንደገና ተመሳሳይ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው ውሳኔ ቢተላለፍም ለአንድ ወር በገላን ከታሰሩ በኋላ ትናንት መለቀቃቸውን ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ተናግረዋል፡፡

ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ጥንቅር ልኮልናል፡፡