የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ200 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠ
ሐሙስ፣ መስከረም 23 2017የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ200 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስገዝ ዪንቨርስቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በራሱ መስፈርት አውዳድሮ የተቀበላቸውን 5ሺህ 300 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በመያዝ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ትምህርት እንደሚጀምር አስታወቀ ። ዩኒቨርሲቲው ከመዘገባቸው ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ለ 200 ተማሪዎች ነፃ የትምህር እድል ተሰጥቷቸዋል።
ለመጀምሪያ ግዜ ዘንድሮ 5 ሺህ 300 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማስተማር በራሱ መንገድ አውዳሮ የተቀበለው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በ 2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው 50 እና ከዛ በላይ ላመጡ ተማሪዎች ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ወደ ዩኒቨርስቲው ለመግባት የተመዘገቡት 11, 939 ተማሪዎች በአዲስ አበባ እና በሀገሪቱ ባሉ 7 የተለያዪ የመንግስት ዪንቨርስቲዎች የመግቢያ ፈተናውን ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉ 5,300 ተማሪዎችን መቀበሉን አስታውቋል ። ከእነዚህ መካከል 200 የሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዋች በ ዩኒቨርስቲው ነፃ የትምህርት እድል እንደተሰጣቸው ተናግረዋል ።
በራሱ ምዘና ብቻ ተማሪዎችን ለመቀበል የወሰነዉ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
በዚህ ዓመት ለከፍተኛ ትምህርት ብቁ ናቸው ተብለው ትምህርት ሚኒስቴር ካረጋገጠላቸው መካካል 11 ሺሕ 939 ተማሪዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመመረጥ ለፈተና ቀርበዋል፡፡ የቅበላ ፈተናው የሚለካው ወደ ዩኒቨርሲቲው የሜገቡ ተማሪዎች የቅድሞ ምረቃ ፕሮግራም ለመክታተል የሚያስችል ብቃት እንዳላቸው የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ባክሄደው የትምህርት ዘመኑ የቅበላ መስፈርት ሴቶች እና የአካል ጉዳተኞችን ከግምት ውስጥ ያካተተ እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጄሎ ኡመር ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስልምና በዓላት አከባበር ላይ ጥናት አካሄደ
በዚህ ስሌት መሰረት የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ ነጥብ አሟልተው በመንግስት ሙሉ ወጪ እንዲሽፈንላቸው ከጠየቁ 4 ሺህ 402 ተማሪዎች መካክል 2 ሺህ 660 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን ማለፋቸው እና ወጫቸውን በራሳቸው ከፍለው ለመማር ካመለከቱት 7 ሺህ 537 ተማሪዎች መካከል ደግሞ 2 ሺሀ 640 ተማሪዎች አብላጫውን ውጤት በማምጣት ዪንቨርሲውን ተቀላቅለዋል ብለዋል፤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት።
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ 66 ፕሮግራሞች ያሉት ሲሆን የተመረጡት ተማሪዎች በፈለጉት የትምህርት መስክ የሚማሩ ይሆናል ያሉት ዶ/ር ጄሎ የህክምና እና የኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮግራሞች በአብዛኛው ተማዎች ዘንድ ተመራጭ መሆናቸውንም ተናግረዋል በክፍያ ማስተማር የሚጀምረው አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዝርዝር የክፍያ መጠኖችን ባያስታውቅም እንደዬየፕሮግራሞቹ ክፍያቸው እንደሚለያይ ተናግረዋል።
ሃና ደምሴ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ