መኢአድ እና ሰማያዊ በጋራ ሊወዳደሩ ነው
ማክሰኞ፣ መስከረም 23 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ። ቦርዱ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ከሞላ ጎደል ማጠናቀቁን እና የምርጫ ቁሳቁሶችም እየተዘጋጁ መሆናቸውን ለዶቼቬለ ተናግሯል።
በዘንድሮው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል። በ1997 የተደረገው ምርጫ ውጤት ባስከተለው ውዝግብ ምክንያት አዲስ አበባ በቦርድ ትመራ ስለነበረ ምርጫ የምታደርገው ከብሔራዊው ምርጫ በተለየ ዓመት ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ