የአውሮጳ ኅብረትና አዲሱ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት
ሐሙስ፣ ጥር 13 2013ማስታወቂያ
የዓለም መንግሥታት፣46ተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በመሆን ትናንት ቃለ መሃላ ለፈጸሙት ለአዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመልካም ምኞት መግለጫዎችን እያስተላለፉ ነው።በዚሁ መግለጫቸውም ከባይደን ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።ለፕሬዝዳንት ባይደንና ለአዲሷ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላለፈው የአውሮጳ ኅብረት የቀድሞውን የኅብረቱንና የአሜሪካን ግንኙነት ማደሻው ጊዜ አሁን ነው ሲል አስታውቋል።የኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን አውሮጳ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ግንኙነታቸውን ለማዳስ ኅብረቱ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ